ህጻናት ለምድ ነው መጥፎ ባህሪ የሚኖራቸው?
ወላጆች የማይወዱት ነገር ህጻናት ለምን ማድረግ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ይቸገራሉ። ህጻናት የሚሰማቸውን ነገር በባህሪያቸው ለማመልከት ይጥራሉ።
ልጅዎት መጥፎ ጸባይ ለማሳየት ምክንያቱን ካወቁ ለየት ባለ አቀራረብ ባህሪ ለመርዳት እንዲችሉ ዘዴን ለማግኘት ያስችላል።
ለመጥፎ ባህሪያቸው ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡
- ትኩረት እንዲያገኙ
- ለየት ባለ ሁኔታ ለመደራደር ችሎታ ስለሚያጥር
- እርዳታ ለማግኘት ማልቀስ
- ያለመግባባት
- ምክንያት በሌለው ደንብ ወይም አስተሳሰብ ላይ
- ደንብን በመርሳትና ከገደብ ሲወጡ ይሆናል።
ገደብን ስለመወሰን
ለህጻናት ገደብ መስጠት ያስፈልጋል። ምርጫ እንዲያገኙ፣ ሀላፊነት እንዲሰማቸውና በጥሩ ሁኔታ እንዲላመዱ በማያሰጋ መልኩ ገደብ ይስፈልጋል። ገደቡ ግልጽ እና የማያቋርጥ መሆን ሲኖርበት ተከታታይ ያልሆነ ገደብ ህጻናት ማድረግና ማድረግ ስለሌለባቸው ነገሮች እርግጠኛ አይሆኑም። ሁሉም መከተል በሚችለው ቀላል ደንቦች ማውጣትና ለነዚህም ምክንያት ማቅረብ ይሆናል። ለደንበ ህገ ገደቡ ሲያወጡ ላቀረቡት ምክንያት ማቅረብና እርግጠኛ መሆን አለብዎት።
በተደጋጋሚ ስለ ደንቦችና ገደቦች ለህጻናት ማስገንዘብ ይገባል።
ደንቦች በመጣስ ሊያስከትል የሚችለው፡
- ወዲያውኑ ሊከሰት ይችላል
- አጭር ወይም ትርጉማቸውን ይሰጣሉ
- ከመጀመሪያው ችግር ጋር ሲቀናጅ
- ሁልጊዜ ለህጻናት ደህንነትና ክብር መስጠት
በሀሳብ መጽናት ነገር ግን ትክክለኛ መሆን።
ልጆችዎን እንደሚከተለው መርዳት፡
- በማዳመጥ ግልጽ ንግግር ማካሄድ
- ስሜታቸውን በማሞገስ
- አለመቀያየር
- የርስዎ ግምት ትክክለኛ ስለመሆኑ ማረጋገጥ
- የርስዎን ጊዜና ክትትል መስዋእት ማድረግ
- ችግራቸውን ሲፈቱ ማበረታታት
- ለጥሩ ጸባያቸው በማድነቅ ማበረታታት ነው።
ያስተውሉ፡
- ሁሉም ህጻናት የተለያዩ ስለሆኑ የተለያየ አስተዳደግ ዘዴ እንደሚያስፈልግ ነው።
- ሁልጊዜ ዘዴው ላይሰራ ስለሚችል ሌላ መንገድ መፍጠር
- የአስተዳደግ ዘይቤ እንደ ህጻኑ እድሜ፣ ችሎታና ፍላጎት መወሰን አለበት።