መናገርና እርምጃ መውሰዱ ሊጎዳ ይችላል
ህጻናትን በምናነጋግርበት ጊዜ አቀራረባችን ስሜታቸውን እንዴት እንደሚነካ ማወቅ ያስፈልጋል።
ብዙጊዜ በመጮህ የመናገር ባህሪ ይኖራል። ታዲያ ለልጅዎ ምን ያስተላልፋሉ?
ለህጻናት የምንናገረው ነገር መልሰው በመድገም ስለማንነታቸው እና ምን ለመሆን እንደሚፈልጉ ሃሳብ ያቀርባሉ።
መጥፎ ጎጂ በሆነ ቃላት የተናገሩት ለብዙ ጊዜ ላይረሳ ይችላል። እንደ ወላጅ መጠን አንዳንድ ጊዜ ከሚያስቡት አንጻር በህጻናት ፊት ይናገራሉ ወይም ድርጉት ይፈጽማሉ። በአጠቃላይ ህጻናት አልፎ አልፎ ለሚከሰቱ ጎጂ ወይም አንጻራዊ ንግግሮች ለብዙ ጊዜ አያስታውሱትም። ስለዚህ ብዙጊዜ አንጻራዊ የሆኑ መልእክቶችን በንግግርና በተግባር ስናሳያቸው በበለጠ ሊያምኑ ይችላሉ።
ህጻናት ያዳምጣሉ፤
መወገድ ያለባቸው ነገሮች፤
ህጻናትን ያለማነጋገር መዝጋት።
ለህጻኑ አንጻራዊ ስያሜ መተቸት ማለት ደንቆሮ ወይም መጥፎ ልጅ በማለት መጥራት እንደ ምሳሌ ይቆጠራል።
ህጻኑን ያለአግባብ መኮነን። ለምሳሌ፡ ይህን ያደረክ አንተ ነህ ማለት፤ እህትህ እንደዚህ ዓይነት ነገር በፍጹም አታደርግም በማለት መናገር።
ለእኔና እናትህ መጣላት መንስሄው ሁልጊዜ አንተ ነህ በማለት።
ፍቅርን መንሳትና ማቋረጥ። ለምሳሌ፡ አንተ ባትወለድ ይሻለኝ ነበር በማለት።
መናገር ሲፈልጉ በረጂሙ መተንፈስ እና መቃወም።
አንድን ህጻን ከሌላው ጋር ማወዳደር።
በሌሎች ህጻናት ፊት ሲናገሩ መስማት ስለሚችሉ መጥፎ አለመናገር።
ህጻናትን ማዳመጥ
ህጻናትን ማዳመጥ ጠቃሚ እንደሆነ ለመግለጽ ይሆናል።
ከልጆች ጋር ጊዜ በመውሰድ ያላቸውን ሀሳብ ማዳመጥ አንዳንዴ ህጻናት አይናገሩም ምክንያቱም አድሉ ስለማይሰጣቸው ነው። በቤተሰብዎ አባላት የሚቀርበውን ሀሳብ በየተራ ለማዳመጥ እድል እንዲፈጠር መጣር ይገባል።
ማዳመጥ ማለት ቃላቶችን ብቻ ማዳመጥ ሳይሆን ቃላቱ ምን ዓይነት ስሜት እንደሚያስከትል ማጣራት ነው።
የተባለን ነገር ማዳመጥ። ለብዙዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ የመናገር ባህሪ ነው። ልጅዎት ምን ሊነግርዎት ይፈልጋል?
በት እግስት ማዳመጥ። ልጅዎት ያለውን ታሪክ እንዲናገር ጊዜ መስጠት። ለማለት የፈለገውን እስኪጨርስ ድረስ አለማቋረጥ ነው።
በጉጉት ማዳመጥ። በልጅዎት አስደናቂ ሁኔታ ላይ ተካፋይ መሆን።
ህጻናት ሃሳባቸውን ለመግለጽ ወይም ከርስዎ ጋር ለመነጋገር ቃላትን በራሳቸው መምረጥ እንዲችሉ መርዳት ነው።