ለህጻናት አእምሮ እድገት የወላጅነት ጠቀሜታ
ለሰው ዘር የአእምሮ እድገት ጊዜ ይወስዳል። ህጻን ሲወለድ ለሕይወት ዋና ጠቃሚ የሆኑ አሠራሮች በአንጎል በኩል ይደራጃሉ – ይህም መተንፈስ፣ የልብ ትርታ አለመቀያየር፣ መጥባት፣ መተኛትን ያካትታል። ሌላው የአንጎል አሠራር ለመዳበር አመታት ይወስዳል።
ስለልጅዎ የአእምሮ እድገት በበለጠ ማወቁ ጥሩ መንገድ ሲሆን ህጻናት እንዴት እንደሚያስቡ፣ እንደሚሰማቸውና አደብ እንደገዙ ለመረዳት ያስችላል። ስለዚህ ህጻናት የተወሰነ የማሰብና ምክንያት የማቅረብ ችሎታ ሲኖራቸው – ታዲያ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት የሚኖራቸውን ስሜቶች፣ አስተሳሰብና ባህሪ ማያያዝ አይችሉም። በነዚህ ጉዳዮች ላይ ሃላፊነት ያለው የአንጎል ክፍል በመጀመሪያ ህጻንነት ጊዜ ‘አይጀምርም’።
የህጻናት አእምሮ እንዴት እንደሚዳብር ስናውቅ ታዲያ ወላጆች ብዙጊዜ….ለምን? የሚለውን ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ ምልክት ይሰጡናል።
ለምን ይህንን ያደርጋሉ?
ለምን አይሰሙም?
ለምድ ነው አንድን ነገር አሁንም አሁንም የምደጋግመው?
ስለአእምሮ እድገት
ለእያንዳንዱ የአእምሮ እድገት ደረጃ ላይ በዘርና በአካባቢ ተጽእኖ ሲያድርበት ነገር ግን በጣም የተለያየ ሚና ይጫወታሉ። በዘር የሚተላለፉት በአብዛኛው ለአንጎል ‘መሰረታዊ የእቅድ ማሰሪያ’ ሃላፊነትን ይወስዳሉ። በአንጎል ውስጥ ያለን ጥቃቅን ነግሮች በማገናኘት ለማጠናከር የሥራ ልምድ ሃላፊነት ይኖረዋል።
በኑሯችን ጊዜ ለሚያጋጥመን ልምድ ምላሽ ለመስጠት አንጎላችን ያለማቋረጥ ይቀያየራል። የህጻናት አንጎል በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በቀላሉ የሚታለል ወይም የሚቀያየር ‘ፕላስቲክ’ ይሆናል። ይሁን እንጂ እኛ ለአዲስ ልምዶች ለመላመድና ለመማር ቅርጽን እየቀያየርን እንደምንቀጥል ሁሉ በሕይወት ዘመን አንጎልም እንደ ፕላስቲክ ሆኖ ይቆያል።
አንጎል የተሠራው ከብዙ ክፍሎች ሲሆን እነሱም የተለያየ ነገሮችን ያካሂዳሉ። ኒውሮን/ነርቮች ‘ማሰሪያ ሽቦዎች’ ሲሆን የተለያዩ የአንጎል ክፍሎችን ያገናኛል። እነዚህ የአንጎል ክፍሎች ግንኙነት መጠንና ምን ያህል የመደራጀታቸው ሁኔታ ለሚያጋጥመን ልምድ እንዴት ምላሽ እንደምናደርግ፣ ስለዝምድና መረዳት፣ ነገሮችን በማስታወስና በመማር ላይ ተፅእኖ እንደሚያሳድር ነው።
የተለያዩ የአንጎል ክፍሎች በተለያየ የእድሜ ገደብና በቅደም ተከተል እንደሚዳብሩ ነው። ስለዚህ በተለያዩ ህጻናት የሚከሰቱ ልምዶች በተለያዩ እድሜዎች ላይ የእያንዳንዱን የአንጎል ክፍል ለማጠናከር ጠቀሜታ ይኖረዋል።
ለልጅዎ የአእምሮ እድገት እርስዎ ዋና ገባሪ እንደሆኑ ነው
ለጋ አንጎሎች ለሚያጋጥም ተመኩሮ በጣም ፈጣን ናቸው። ለህጻናት ቀደም ብሎ የሚያጋጥማቸው ሁኔታዎችና አካባቢው በህጻናት የአንጎል እድገት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳድርባቸዋል። ለዚህ ነው ወላጆች በህጻናት አንጎል ላይ ተፈጥሯዋዊ የወላጅነት ቅርጽ ለማስተካከል ሊረዳ የሚችለው።
በህጻናትና በወላጆቻቸው የሚደረገው ድጋፍ፣ እንክብካቤና የማያቋርጥ ዝምድና ግንኙነት ጤናማ አንጎል ለማዳበር ዋና ጠቃሚ ናቸው።
ጤናማ አንጎል እንዲፈጠር ማበረታታት
ለታዳጊ ህጻንት በመነካካት፣ በማቀፍ፣ ምቹነት በመፍጠር፣ በማወዛወዝ፣ በመዘመርና በማነጋገር አስፈላጊ የሆነውን ነገር አለማቋረጥ ማቅረቡ ለአንጎላቸው እድገት ይጠቅማል።
ከህጻንነት ጊዜ ጀምሮ ለልጅዎ ማነጋገርና ማንበብ።
ልጅዎ አዲስ ችሎታን በሚያገኝበት ጊዜ ሁኔታውን ለመደጋገምና እንዲላመድ ብዙ እድሎችን መፍጠር ነው። ይህ በአንጎል ውስጥ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ይረዳል።
በተቻለዎ መጠን ከልጆች ጋር መጫወት ነው።
ህጻናት በአካል እንዲወሳወሱ፣ ማለት እንደ መንከባለል፣ ብስክሌታ መንዳት፣ ኳስ መጫወት፣ ምዝለልና መሮጥ እንዲችሉ ማበርታታት ይሆናል።
ህጻናት ለወደፊት ተስፋ እንዲያድርባቸው መርዳት ነው።
የማያቋርጥ አሰራር ዘዴዎችን መፍጠር።
ልጅዎ ከአጋጠማቸው አዳዲስ ልምዶች ጋር ሙከራ እንደሚያደርጉ አይነት አድርገው ማነቃቃትና ማበረታታት ነው።
ህጻናት በተለያየ የእድሜ ገደብ ለማድረግ በሚችሉት ጉዳይ ላይ ግልጽ መሆን። እስከማይሳካለት ድረስ አለመገፋፋት።
ልጅዎ ቀለል ባለና ደረጃ በደረጃ ልምድ በማግኘት ልምድ እንዲያገኝ መርዳት።
አንድ ልጅ ካልተሳካለት አለመተቸትና ላደረጉት ጥረቶች አድናቆትን መስጠት ይሆናል።
ታዳጊ ህጻናትን ለለውጥ ማዘጋጀት ነው።
ህጻናት በራሳቸው አቅም አዲስ ልምድ እንዲያገኙ ማድረግ እንጂ እርስዎ እንደፈለጉት አይሁን።