ልዩነት ስለመቀበል

ሁለት ሰዎች በምንም ዓይነት አንድ እንደማይሆኑ ነው።

በቅርጽ፡፣ በአነጋገርና በአለባበስ አንድ ሊሆኑ አይችሉም። በልምድን፣ በባህል፣ በእምነትና በሃይማኖት ልዩነት ሊኖራቸው ይችላል። የተለያየ ችሎታ ሊኖራቸው ይችላል። በተለያየ ቤትና የቤተሰብ ጥላ ስር ሊኖሩ ይችላሉ።

ህጻናት የነዚህ ልዩነቶች መኖር ችግር እንዳልሆነ ማወቅ ያስፈልጋል።

ብዙጊዜ ህጻናት በራሳቸውና በሌሎች ስለሚገነዘቡት ልዩነቶች ይጠይቃሉ።

  • "ሰውየው በዊልቸር የሚሄድ ለምድ ነው?"
  • "ሰውየው ከእኔ የተለየ ቆዳ ያለው ለምንድ ነው?"
  • "ሰውየው እነዚህን የሚያስቅ ልብሶች የሚያደርገው ለምንድ ነው?"

ታዳጊ ህጻናት የሌሎችን ልዩነቶች ያለምንም ጥያቄ መቀበል ይኖርባቸዋል። የተለያየ አመጣጥ ወይም ችሎታ ካላቸው ወይም የተለያየ ቤተሰብ ካላቸው ህጻናት ጋር ጓደኛነትን መፍጠር።

ህጻናት እያደጉ ሲሄዱ የልዩነት ጥቅምን ከወላጆቻቸው መማር ይችላሉ። እርስዎ በባህልና በሌላ ያለዎትን አቀራረብ ለታዳጊ ህጻናት ልዩነት ካላቸው ሌሎች ህጻናት ጋር ለመግባባት ተጽዕኖ ያሳድርባቸዋል።

የሚኖርዎትን ልዩነት ተቀባይነት እንዳለው ማሳየት ነው። ስለሌሎች አስተሳሰብ ምን ያህል ቻይና ታጋሽ ነዎት? በተለያዩ ልምዶች፣ እምነቶና ባህላዊ አመጣጥ ለማስተናገድ ምን ያህል ትእግስተኛና አስመሳይ ነዎት? የግለሰብን ፍላጎት ምን ያህል ክብርና ዋጋ ይሰጡታል? ከርስዎ ልዩነት ካላቸው ሰዎች ጋር ያለን ልዩነት እንዴት መግለጽ ይችላሉ?

ልዩነት መቀበል ማለት የእኛን ተመሳሳይነትና ልዩነት በመረዳት የእያንዳንዱ ሰው አቀራረብ በመከባበርና መርዳዳት መሆን ይኖርበታል።

ተቀባይነት ባለው ነገር ስለማበረታታት

ልጅዎት የቤተሰቡን ታሪክና አመጣጥ እንዲረዳ ማድረግ። በቤተሰብዎ ውስጥ ስላለው ልዩነት ለልጅዎ መንገር። እያንዳንዱ ሰው ጥሩ በሆነ ነገር ላይ የራሱ የሆነ የሚወደው፣ የማይወደውና የሚፈልገው ሁኔታ ይኖራል።

ልጆች ስለሚኖረው ግንዛቤ፣ ጥያቄ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ እንዲናገር ማበረታታት ነው። ልጅዎት የሌሎችን ስሜትና ፍላጎት ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት መርዳት፣ ይህም እራስን በሌላ ጉዳይ ውስጥ እንደማስገባት ይቆጠራል።

ልጅዎት ያለውን ልዩነት በአድናቆት ማክበር እንደሚኖርበት ለማሳወቅ መረዳት ይሆናል። ልጅዎ የተለቪዥን ፕሮግራም በመከታተል ወይም ስለሌሎች ሰዎችና ቦታዎች የሚገልጹ መጽሐፍትን በማንበብ ለሌሎች ባህሎችና ሰዎች በማሳየት ማስተዋወቅ ሲቻል ይህም በአካባቢ ማህበረሰብ በሚደረጉ ክብረ በዓላት ላይ ተሳትፎ በማድረግ ይሆናል።

Listen
Update Required To play the media you will need to either update your browser to a recent version, enable javascript or update your Flash plugin.