ህጻናት ማጫወት የወላጆች ሥራ ይሆናል

ህጻናት ከሚፈልጉት ነገር ጨዋታ አንደኛው ጠቃሚ ነገር ነው። ከልብ ከተጫወቱ ያስቃል።

ስለዚህ ህጻናት በአብዛኛው ጊዜ ሊማሩ የሚችሉት በጨዋታ መልክ ይሆናል።

በጨዋታ ሁሉንም የጤና እድገቶች ማሟላት የሚችሉት፡

  • በመሮጥ፣ መራገጥ እና ኳስ መወርወር ህጻናት ሚዛናቸውን ለመጠበቅና ለመቆጣጠር ይረዳል።
  • መዘመርና በግጥም መጫወቱ ቋንቋን ያዳብራል።
  • በእንቆቅልሽ ጨዋታ ችግርን በመፍታት የህጻናትን ችሎታ ያዳብራል።
  • ሲጫወቱ ተራ መጠበቅ እና የመዋዋስ ልምድ ችሎታና እራስን ለመቆጣጠር እንዲችሉ ይረዳል።

ህጻናት መሥራት እንዲችሉ እና ስሜታቸውን ለመግለጽ ጨዋታ ጠቃሚው መንገድ ይሆናል። ህጻናት ሲጫወቱ መከታተልና ተሳትፎ በማድረግ ልጅዎት ምን እንደሚሰማው ወይም እንደሚያስብ ለመገንዘብ ይችላሉ።

ህጻናት ሲጫወቱ ወላጆች ወሳኝ የሆነ የሥራ ድርሻ ይኖራቸዋል።

ከልጅዎ ጋር አብረው ሲጫወቱ አወንታዊ ግንኙነት በመፍጠር አስደሳች ሁኔታ መፍጠር ይገባል።

ከልጅዎ ጋር አብረው ሲጫወቱ አዲስ ችሎታ እንዲያዳብር እድሉን ከፈቱለት ማለት ነው። ህጻናት አወንታዊ የሆነ ድጋፍ ማግኘት የሚችሉት በወላጆች ተቀባይነት ሲኖራቸውና ብርታት ሲደረግላቸው ነው። ስለዚህ ህጻን ከወላጅ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ በየቀኑ ለተወሰነ ጊዜ አብሮ ስለመጫወትዎ ማረጋገጥ ይገባል።

ከህጻናት ጋር ሲጫወቱ ጨዋታው ከልጅዎ እድሜ ደረጃ ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለበት። በጣም ቀላል ከሆነም ልጅዎ ይሰለቸዋል። በጣም ከባድ ከሆነም ሊፈራና ተስፋ ሊቆርጥ ይችላል። ልጅዎ በራሱ ጨዋታውን እንዲመራ ማድረግ። ከዚያ በላይ አለማድረግ።

በጨዋታ ላይ ችግር እንዳይፈጠር ማረጋገጥ

አብረው ሲጫወቱ ልጅዎ ይውትኛውን ጨዋታ እንደሚፈልግ መጠየቅ ነው።

ለጨዋታ በቂ ጊዜ መስጠት።

ከታዳጊ ህጻናት ጋር አለመወዳደር፡፡ ይህ ጨዋታውን እንዲጠሉት ሊያደርግ ይችላል።

ልጅዎት እንድን ጨዋታ መደጋገም ከፈለገ ትእግስት ያስፈልጋል። ደስተኛ ሆኖ መከታተል ነው።

ሲጫወቱ የሆነ ውጤት ቢመጣም በነሱ ጥረት ላይ አለመቃወም።

በማንኛውም ጊዜ በጨዋታ የሚጠመዱበትን ሁኔታ መፈለግ ይገባል። ለምሳሌ፡ ልጅዎት በግጥም ሲዝናና ወይም ሲዘምር እንዲሁም በየቀኑ በሚያደርጋቸው ሥራዎች ማለት አልጋ በማንጠፍ ላይ አብሮ ተሳትፎ ማድረግ።

Listen
Update Required To play the media you will need to either update your browser to a recent version, enable javascript or update your Flash plugin.