የእንጀራ አባት ወይም እናት ያለበት ቤተሰብ ውስጥ ልጆችን ማሳደግ

የእንጀራ አባት ወይም እናት ያለብት ቤተሰብ እየተለመደ መጥቷል።

እያንዳነዱ የእንጀራ እናት ወይም አባት ያለበት ቤተሰብ ልዩነት አለው። ልጅ በሚያሳድጉበትም ጊዜ አሰቸጋሪ ሁኔታዎችም ጥሩ ሁኔታዎችም ያጋጥሟቸዋል። ሁሉም የእንጃራ አባት ወይም እናት አዲሱን ቤተሰባቸውን መስረተው በጋራ መኖር ሲጀምሩ የጎላ የኑሮ ለውጥና የኑሮንም ሁኔታ ማሰተካከል ይኖርባቸዋል። በዚህም ጊዜ ልጆችና ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ትኩረት ሊስጠው የሚገባው ዋና ጉዳይ ነወ።

ልጆች በወላጆቻቸውም ሆነ በእንጀራ አባታቸው ወይም እናታቸው በጣም የተወደዱ መሆነቸውና ለወላጆቻቸው መለያየት የእነሱ ጥፋት እንዳልሆነ እንዲያውቁ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። እያንዳንዱም ወላጅ ሰለ ሌሎቹ ልጆች ውላጆች መልካም ነገር ብቻ መናገራቸውን እርግጠኛ መሆን ይኖረባቸዋል። ወላጆች በተቻላቸው መጠን ብዙ ጊዜ ከልጆቻቸው ጋር ማሳለፍ አለባቸው። ልጆች ከውላጆቻቸው ጋር ኖሩም አልኖሩም ምንጊዜም ቢሆን እናታቸውም ሆነ አባታቸው እንደማይለይዋቸው ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ከልጆቻቸው ጋር የማይኖሩም ወላጆች ለልጆቻቸው ሊያበረክቱት የሚችሉት ከፍተኛ ሚና አለ። ልጆች ሰለ አዲሱ ቤተሰባቸው የሚያሳሰባቸውን ሃሳብ ሊያካፍሉ ይችሉ ይሆናል። በዚህም ጊዜ ልጆችን ማዳመጥና ተገቢውን ድጋፍ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ። ልጆች አዲሱን ኑሮአቸውን ከእንጀራ አባት ወይም እናት እና ለጆች ጋር ሲጀምሩ እንክብካቤ፡ የተደላደለ የኑሮ ሁኔታና እና አስተማማኝ ግኑኝነት ከሁለቱም ወላጆቻቸው ጋር ማድረግ ይኖርባቸዋል ይህም ከአዲሰ ከማያውቁት ጎልማሳና ልጆች ጋር የእንጀራ አባት ወይም እናት ባለበት ቤተሰብ አዲሰ ግኑኘነት ሲጀመር ይረዳቸዋል።

የእንጀራ አባት ወይም እናት ያለበት አዲሰ ቤተሰብ ሲመሰረት መታሰብ የሚገባቸው ጉዳዮች፡

  • አዲሰ ከሚኖሩት የትዳር ጋደኛቸው ልጆች ጋር ግኑኝንትነ ማዳበር
  • አዲስ የተመሰረተው ቤተሰብ ውስጥ የሚኖሩት የእንጀራ ልጆች እርስ በርሳቸው ጥሩ ግኑኝነት እነዲያዳብሩ ድጋፍ መስጠት።
  • የልጅ አስተዳደግ ዘይቤአቸው ተመሳሳይ ወይንም የተለያየ ቢሆንም አዲሰ በመሰረቱት ቤተሰብ ልጆችን አንዴት በጋራ ማሳደግ እንዳለባቸው መስማማት።

ለጥቂቶች ልጆች የእንጀራ እናት ወይም አባት ያለበት ቤተሰብ ውስጥ ለመኖር የሚደረገው የሽግግር ወቅት አስቸጋሪ ነው። ልጆች፡

  • ቀደም ሲል በቤተሰብ ውስጥ የነበራቸውን ሁኔታ ሊያጡ ይችላሉ
  • እንደቀድሞው የግላቸው መኝታ ቤት ላይኖራቸውና አነድ መኝታ ቤት ከሌላ ሰው ጋር መጋራት ይኖረባቸው ይሆናለ።
  • ቀድሞ ወላጃቸውን በግላቸው ሲያገኙ እንዳልነበር አሁን ግን ከሌሎች ጋር መጋራት ይኖርባቸው ይሆናል።
  • ቀደም ሲል የነበራቸው ቤተሰብ እንደገና እንዲመለስ ይፈልጉ ይሆናል
  • ከቀድሞ መኖሪያ ቤታቸው ፡ ጓደኞቻቸውን ትተው ፡ የቀድሞ ትምህርታቸውን አነዲሁም ሌሎች የተላመዷቸውን ወላጃቻቸውን ተለይተዋል

ሆኖም ልጆች ከእንጀራ አባት ወይም እናት ያለበት ቤተሰብ ጋር በመኖራቸው የጎላ ጥቅምም ሊኖራቸው ይችላል።

  • ወላጅ እናታቸው ወይም አባታቸው አዲሱ በመሰረቱት ቤተሰብ ከቀደሞ ኑሮአቸው በበለጠ ደስተኛ ናቸው።
  • እንክብካቤ ሊያደርግ የሚቸል ተጭማሪ ጎለማሰ ሰው አያትን ጭምር ሊኖር ይችላል
  • ለጆች አዲሰ ወንድምና እህት ይኖራቸዋል
  • እንደገና የቤተሰብ አባል ሆኖ ለመኖር ጥሩ አጋጣሚን ይፈጥራል

በዚህ የመሸጋገሪያ ወቅት ወላጆችና የ እንጀራ አባት ወይም እናት ለጆችን ሊረዱ የሚችሉነት ብዙ መንገዶች የኖራሉ።

ልጆች ያላቸውን ስሜት በሚያሳዩት ጸባይ ይንጸባረቃል። የልጆች ጸባይ በመጥፎ መልኩ መለወጥ የሚያሳየው ልጆቹ እንዳልተሰማማቸውም ነው። በዚህም ጊዜ ልጆች የሚናገሩትን ቃላትና የሚያሳዩትን ጸባይ እንዲሁም የሚያሳሰባቸውን ጉዳይ ልብ በሎ መገንዝብ ያስፈልጋል።

በዙዎቹ ልጆች በኑሮ መሸጋገሪያ ወቅት ችግር ሲገጥማቸው የሚያሳዩት ጸባይ፡

  • የእደግት ደረጃቸው መቀነስ ወይም ወደ ልጅነት መመለስ እነደ አልጋ ላይ ሽንት መሽናትና እንደ ሕጻን ልጅ መናገር የመሳሰሉት ጸባዮች
  • መቃዠትና እንቅልፍ ማጣት
  • ትምህረት ቤት መቸገርና የትምህርት ችሎታቸው መቀነስና ቀደም ሲል የሚካፈሉበት ልዩ ልዩ ድርጊቶች ውስጥ ለመሳተፍ አለመፈለግ
  • ተቆጭና አኩራፊ መሆን

እነደ ወላጅና እንጀራ አባት ወይም እነጀራ እናት ማድርግ ያለብን

  • ልጅዎን ማዳማጥ
  • ሁኔታዎቸን ከልጆቹ አመለካከት አንጻር መረዳት
  • አዲሰ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ልጆችን ሁሉ ሰለ ሰሜታቸው ሆን ችግራቸው እንዲናገሩ ማበረታታት
  • ግንኙነታቸው እንዲዳብር መደገፍ ሆኖም እነርሱ በሚፈለጉት የግኑኝነት ደረጃ እንዲዳበር ማድረግ
  • በቤተሰቡ ውስጥ ለሚደረጉ ነገሮች አዲሰ የተመሰረተው ቤተሰብን ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ማናቸውም ልጅ አስተማማኝ በሆነ መልኩ ድርጊቶችን ለማከናውን የሚያስችል ቅደም ተከተል ማዘጋጀት
  • እያንዳንዱን ልጀ ብቻ ለብቻ ለማነጋገር የሚያሰችል ጊዜ መስጠት
  • ለጆቾን እንደምታፈቅሯቸውና ሁሉጊዜም ከእነርሱ ጋር እንደምትሆኑ ማስታወስ