ስለመጀምሪያ ዓመታት

በህጻን ሕይወት ላይ እነዚህ የመጀምሪያ ዓመታት ለምድ ነው አስፈላጊ የሆኑት?

ከትውልድ እስከ ሶስት ዓመት እድሜ ያለው ጊዜ፣ ልጅዎ በፍጥነት የሚማርበትና የሚያድግበት ጊዜ ነው።

በነዚህ የመጀመሪያ ዓመታት የህጻኑ አንጎል የሚዳብርበት ሁኔታ ነው። ታዲያ በነዚህ የመጀመሪያ ሶስት ዓመታት የልጁ ሕይወት፣ አንጎል በሚገባ የሚዳብርበትና እንዲሁም ለመጪው እድገት የመሸጋገሪያ መሰረት ይጥላል።

ማንኛውም ስለምናደጋቸው፣ ለምንናገረው፤ ለምናስበውናለሚስማማን ነገሮች በልምድ የሚመጣ ቢሆንም መልእክቱ በአንጎል ይተላለፋል። ለመውደድም ሆነ ለመሳቅ፣ ለማልቀስ፣ ጥሩ ለመስማትም ሆነ ለመደናገር አንጎል ሁሉንም እንድንረዳ ይፈቅድልናል።

በእድገት ላይ ስላለ አንጎል

ህጻን ሲወለድ በመቶ ቢልዮን የሚቆጠር ሴል ህዋሳት ይኖረዋል። ይሁን እንጂ አንጎል ግን በተሎ አይዳብርም። በመጀመሪያ ጥቂት ዓመታት ውስጥ የህጻን ሴሎች ህዋሳት እየዳበሩ ይመጣሉ። እንዲሁም በህጻኑ አንጎል ላይ አስፈላጊ የሆነ ግንኙነት በመዳበር የልጅዎ ስሜታዊ፣ ሕብረተሰባዊ፣ ስነ-ፍልጠት አሰራር እየዳበረ ይመጣል።

በነዚህ የመጀመሪያ ዓመታት የልጅነት አንጎል በአካባቢው ላይ ጥላቻ ያሳድርበታል።

በአካባቢው ምን እንደሚደረግ አንጎል በመንገር ይህም በህዋሳዊ አካላት ማለት እንደ ዓይን፣ ጀሮ፣ ምላስና ቆዳን በመጠቀም ነው። ላጋጠመን የሆነ ችግሮች በህዋሳት ተጣርቶ ያልፋል። የእኛ ህዋሳት በአንጎል ላይ ላጋጠመን ልምድ ሆነ መረጃዎች በመረዳት መልስ የሚሰጥበትን መልእክት ያስተላልፋሉ።

በነዚህ የመጀመሪያ ዓመታት ውስጥ የወላጅ ድርሻና አስፈላጊነት

በነዚህ የመጀመሪያ ዓመታት ውስጥ በህጻንና ወላጅ መካከል ያለው ግንኙነት በመዳበር በህጻኑ አንጎል ላይ በተለያየ መንገድ ችግር እንደሚከሰት በምርምር ጥናት የተረጋገጠ ነው።

በነዚህ የመጀመሪያ ዓመታት ህጻናት በፍቅርና እንክብካቤ ከተያዙ ታዲያ ለወደፊት በኑሮ ሕይወታቸው ላይ እምነት ያሳድርባቸዋል። እንዲሁም የመማር አቅማቸውና ችሎታ የበረታ ይሆናል።

ትናንሽ ህጻናትን በበለጠ እንዲያድጉና እንዲማሩ ብዙ ክንክንና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ነው።

ትላልቅ ህጻናት በራስ የመተማመንና እርስን የመጠበቅ መንፈስ እንዲኖራቸው ሲያደርግ፤ ይህም ከወላጆቻቸው ጋር ያለው ዝምድናና ግንኙነት አወንታዊ ሲሆን ብቻ ነው።

ይህ አወንታዊ ዝምድና እና ግንኙነት በሕይወታቸው ላይ ለሚያጋጥማቸው ችግሮች እንዲወጡት ሊያግዛቸው ይችላል።

በነዚህ የመጀመሪያ ዓመታት ለሚጠፋው ጊዜ፡

  • ልጅዎን እንዲያቅፉና እንድታነሳሳቸው
  • እንዲያነጋግሯቸውና ፈገግታ እንዲሰጧቸው
  • የሚያዙትንና የጠየቁትን ተቀብሎ መልስ ለመስጠት
  • ልጅዎ አዲስ ልምዶችና የወደፊት እድላቸውን እንዲጠበቅ ማድረግ
  • የልጅዎ መብትና ደህንነት የጠጠበቀ እንዲሆን ማድረግ ነው።
Listen
Update Required To play the media you will need to either update your browser to a recent version, enable javascript or update your Flash plugin.