በልጅዎ ላይ ‘ማተኮር/Tuning in’

ይህ አትኩሮት ወላጆች የልጆቻቸውን ስሜትና አስተሳሰብ ምን እንደሆነና ልጆቻቸው ምን እንደሚፈልጉ ለማወቅ የሚያስችል ዘዴ ይሆናል። በርስዎና በልጅዎ መካከል የማያሰጋ፣ አወንታዊና ደጋፊ የሆነ ግንኙነት ለመፍጠር የአትኩሮ/‘Tuning in’ ማድረግ መሰረታዊ ነው።

ህጻናት ያላቸው ልምድና ስሜት በወላጆች በኩል እንደታወቀላቸው ለመረዳት ይህ አትኩሮት ሲረዳ ታዲያ በዚህ መንገድ ወላጆች ምላሽ እንደሚሰጡ ነው።

ወላጆች አትኩሮ እንዳደረጉ ህጻናት መናገር ይችላሉ። ህጻናት የርስዎን ፍላጎት እንዳወቁና እንደተቀበሏቸው በዚህ መንገድ ያረጋግጣሉ። ይህ ከልጅዎ ጋር ጥልቀት ያለው የግንኙነት ደረጃን በመፍጠር ታዲያ ህጻናት በሚያድጉበት ጊዜ አወንታዊ የሆነ መድረክ ይገነባሉ።

እርስዎ አትኩሮት በሚያደርጉበት ጊዜ የልጅዎን ስሜታዊና ባህሪያዊ ምልክቶችን ማንበብ እንደሚችሉና በአግባቡ ምላሽ መስጠት ይችላሉ። ህጻናት ላቀረቡት ምላሽ ማግኘቱን ሲረዳቸው ታዲያ በራስ እምነት የማሳደርና አወንታዊ አመለካከት ይኖራቸዋል።

ህጻናት ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ በድምጽ ግንኙነት ሲፈጥሩ፣ ይህም (በማልቀስ፣ በድምጽ፣ በመጮኽ) የገጽታ መግለጫዎች (በዓይን ማየት፣ በፈገግታ፣ ፊትን በማጨማደድ) እንዲሁም ምልክት በመስጠት (በሚያስጨንቅ ወይም በሚያስደስት ላይ እግርን በማንቀሳቀስና ማሳየት) ይሆናሉ። ልጅዎ ንግግር ባልሆነ ምልክት ግንኙነት ሲጀምር ማየት፣ ይህም በዓይን መገናኘት፣ በፊት ላይ እንቅስቃሴ፣ ድምጽ በማሰማት፣ በምልክትና ለሚሰጡት ምላሽ ጊዜና ፍላጎትን ማሳየት ይሆናል።

ልጅዎ እያደገ ሲመጣ ትኩረት ማድረጉ በሁለቱም ማለት በቃላትና በምልክት ግንኙነቶች ላይ ይሆናል።

ለልጅዎ ማወቅ ሲጀምሩ

በአዲስ ልጅዎ ላይ ትኩረት ማድረጉ ህጻኑ ድህንነት እንዲሰማውና እንደተወደደ የማረጋገጫ ምልክት ይሆናል። ልጅዎ በሚያለቅስበት ጊዜ አትኩሮ ማየቱ ታዲያ ለመራቡ/ቧ፣ ለመድከም፣ የሚቀየር ነገር ካስፈለገ ወይም ለመታቀፍ እንደፈለገ ለማወቅ ይረዳል።

በታዳጊ ልጅዎ ላይ ትኩረት ማድረጉ እሷ/እሱ ጸጥ ያለ ጊዜ ከፈለጉ፣ መቆያ ምግብ ወይም የእንቅስቃሴ ለውጥ ከፈለጉ ለማወቅ ይቻላል። በሁለት ዓመት ልጅዎ ላይ ያለ ምክንያት ሲበሳጭ ትኩረት ማድረጉ በተወሰነ ገደብ ምላሽ መስጠት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊበሳጭ ያደረገውን ስሜታዊ ሁኔታ ምን እንደሆነ መረዳት ይሆናል። ልጅዎ ደክሞታል፣ ተበሳጭቷል ወይም ተጎድቷልን?

ትኩረት ማድረግ መቻሉ ከትእግስት፣ ልምድና ልጅዎን በሚገባ ከማወቅ ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነው።

አትኩሮት ማድረግ/Being ‘tuned in’

ያስተውሉ፣ እያንዳንዱ ህጻን በዚህ ዓለም ፍላጎቱን የሚገልጽበት የራሱ የሆነ የመገናኛ ዘዴ መለያ ይኖረዋል።

ልጅዎን በሚገባ ማስተዋል። የርስዎ ህጻን ምልክት ለመስጠት/‘tick’ ምን እንደሚያደርግ መማር ነው።

ስለልጅዎ ሰውነት ላይ ስለሚከሰቱ ሁኔታዎች፣ ተፈጥሯዊ ግላዊ አመል መረዳትና መልመድ ይሆናል። ልጅዎ ስለመራቡ እንዴት ያውቃሉ? ለመድከሙ እንዴት ያውቃሉ? የእርስዎን ትኩረት እንደፈለገ እንዴት ያውቃሉ? የርስዎን ማግኘት ለማረጋገጥና ምቾት ለማግኘት እንደፈለገ እንዴት ያውቃሉ?

የልጅዎን እንቅስቃሴ፣ የድምጽንና ያላቸውን የእንቅስቃሴ መጠን እንዲለውጡ በንቃት መተባበር አለብዎ።

ስለልጆችዎ ጥንካሬና ፍቃደኝነት መማር ይገባል። በሚደሰቱበት ጊዜ እንዴት ያሳዩዎታል? በቀላሉ ይበሳጫሉን? በሚበሳጩበት ጊዜ ዝም ይላሉን?

ልጅዎ ምልክት ሲያደርጉ፣ ሲመለከቱና ድምጽ ሲሰጡ ምላሽ መስጠት። ክንዱን ወደላይ ሲያነሳልዎት ያንሱት፣ ይሳሙት እንዲሁም ቀላል የሆነ ቃላት ይጠቀሙ። “ለመነሳት ትፈልጋለህ”።

ልጅዎን ያነጋግሩ እንዲሁም ያዳምጡት።

የልጅዎን ስሜት ማክበርና ግምት ውስጥ ማስገባት።

የርስዎን የአካል እንቅስቃሴ መልእክት ማወቅ። በንግግርና በምልክት የሚያደርጉት ግንኙነት ከህጻኑ ጋር አንድ አይነት ነውን?