የህጻናትን ባህሪ ስለማስተካከል

ህጻናት ሲወለዱ መጥፎ እና ጥሩ ባህሪ የትኛው ንደሆነ ለይተው አያውቁም። በአካባቢው ባሉ ሰዎችና የርስዎን ጠባይ ይከተላሉ ታዲያ ወላጆች እንዴት አድርገው ልጆቻቸውን ስለሚንከባከቡ፡

ራዕይና ጥሩ ጠባይ መከተል እንዳለባቸው ይወስናሉ። እነዚህ ሀሳቦች ከግቡ ለማድረስ በየጊዜው የባህሪ ለውጥ ይታያል።

ጎልማሳ አዋቂ ሰዎች እነሱ ባደጉበት መንገድ ህጻናትን ማሳደግ ፍላጎታቸው ይሆናል። የአስተዳደግ ሁኔታን መቀየር ከፈለጉ ለወላጆች ጊዜ፣ ጥረትና መስዋእትነትን እንደሚጠይቅ ነው። ስህተት ለመፈጸም በራስዎ መፍቀድ ይኖርብዎታል።

ስነ-ስራአት ከቅጣት ጋር ስለመቃረን

በዛሬ ጊዜ ወላጆች ልጆቻቸውን ስነስርዓት ለማስያዝ እንደሚፈቀድላቸው ተደርጎ ይሰማቸዋል።

አንድ ህጻን በዚህ ዓለም ያለውን ሁኔታ በሚማርበት ጊዜ ለደህንነቱ ሲባል ስነስርዓት መያዝ እንደሚያስፈልገው ነው።

ስነስርዓትና ቅጣት እንድ ዓይነት ነገሮች አይደሉም። ዲሲፕሊን ስርዓት ላቲን የመጣ ቃል ሲሆን ማስተማር ማለት ነው።

ቅጣት ማለት ተቀባይነት ለማይኖረው ጸባይና ባህሪ እርምጃ ሲወሰድ ነው። ህጻናት በቅጣት እርምት ወይም ተቀባይነት ያለው ባህሪ መያዝ ያልተለመደ ጉዳይ ነው።

ስነስርዓት ማስያዝ ዓላማ ማለት ህጻናት በትምህርት ተቀባይነት ባለው መንገድ መሰረት ለሚያሳዩት ባህሪ ሀላፊነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው። ህጻናት በሚያድጉበት ጊዜ በበለጠ እራሳቸውን ስርዓት ያስይዛሉ።

እንዴት አደብ መያዝ እንዳለባቸው በመረዳት ጸባያቸውን በራሳቸው መቆጣጠር ይችላሉ። ራስን ስርዓት ማስያዝ የሚመጣው በጎልማሳ አዋቂ ሰውና በአሳዳጊ የትምህርት ችሎታ ይሆናል።

ጥሩ ስርዓት ሊመጣ የሚችለው በርስዎና በልጅዎት መካከል ባለው ግንኙነት ሲሆን ይህም የልጅዎ ፍላጎት ሲኖር ውጤቱ በበለጠ ያስደስታል። ውጤታማ ስርዓት ከደንቦች መከተል ጋር የሚመጣ ሲሆን ደንብ ሲጣስ ምን እንደሚያስከትል በመረዳት ይሆናል።

የአካል ቅጣት ምን ያስከትላል?

ውጤታማ ያለው ስርዓት ለማስያዝ ያለምንም ድብደባ ወይም አካላዊ ቅጣት ሊመጣ ይችላል።

በድብደባ መቅጣት ችግሩን እንዲያግት ምክንያት ይሆናል። ለምሳሌ፡ አንድን ህጻን በእጅ ወይም በሆነ ነገር መምታት በድብደባ ቅጣት ለህጻኑ እንክብካቤ ወይም የህጻኑን ክብርነት አይገልጽም።

በድብደባ ቅጣት ለህጻኑ መናቅ እና የሚኖረውን ፍቅርና ድህንነት ማጉደል ይሆናል።

ስለዚህ ህጻኑ ሁልጊዜ ድንጉጥ፣ ፈሪና አመጸኛ ሊሆን ይችላል። በድብደባ ቅጣት ማድረጉ ችግር ሲፈጠር ብድብደባ መፍትሄ ማግኘት እንደማይቻል ህጻናት ሊማሩ ይችላሉ።

አንድን ህጻን በመምታት ማስተማሩ ተቀባይነት የሌለው ዘዴ ነው። ይህም ሁኔታውን ከማሻሻል ፋንታ ያን መጥፎ ተግባር እንዲደጋግም ያደርጋል።

ብዙጊዜ ህጻናት ከተመቱ በኋላ ይበሳጫሉ ወይም ይናደዳሉ፤ ለምን እንደተመቱም ይረሱታል።

ህጻናት የእርስዎን ተግባር ባህሪ መከተል ይማራሉ። ህጻናትን ለማናገር በሚፈልጉበት መንገድ ማነጋገር። እነርሱ ስነስርዓት እንዲኖራቸው እንደሚፈልጉት ሁሉ እርስዎም በጠባይ ረጋ ብለው ማነጋገር ነው።

Listen
Update Required To play the media you will need to either update your browser to a recent version, enable javascript or update your Flash plugin.