ወንድማማቾች እና እህታሞች
ወንድማማቾች እና እህታሞች በጣም ጓደናሞች እና እንደ መጥፎ ጠላት ሊሆኑ ይችላሉ። እያንዳንዳቸው የሚኖራቸው ስሜት እንደ እድሜ ደርጃ እድገት ሊቀየር ይችላል።
ወንድማማቾች እና እህታሞች ሊታረቁና ሊጣሉ ይችላሉ። ይህ የተለመደ ሲሆን ህጻናት ክሌላው ጋር የመግባቢያ ዘዴ ይሆናል።
እንደዚህ ዓይነት ባህሪያት በተለያየ ምክንያት ሊፈጠር ይችላል፡
- አንዳንድ ጊዜ ለሁሉም ህጻናት አንድ ዓይነት እንክብካቤ መስጠት አይቻልም። ወላጆች በእያንዳንዱ ህጻን ለሚቀርብ ፍላጎትና የግል አቀራረብ እንደ ሁኔታው ማስተናገድ ይኖርባቸዋል።
- ለወንድማማችና እህታሞች የተለያየ ሀሳብና ጸባይ ማሳየት የተለመደ ጉዳይ ነው። እንዲሁም ህጻናት በማንኛውም ጊዜ ተቃውሞ ማሰማት የተለመደ ጉዳይ ይሆናል።
- ብዙጊዜ ወንድማማችና እህታሞች የወላጅን ትኩረት ለመሳብ ሊጣሉ ይችላሉ።
- ብዙጊዜ ህሳናት አለአግባብ በመሰላቸው ነገር ላይ ይከራከራሉ።
ለወንድምና እህት መልስ አሰጣጥ
የእያንዳንዱን ህጻን ፍላጎትና መብት በተናጠል ክብርና ዋጋ መስጠት። አንጻራዊ ከሆነ ነገር ጋር አለማወዳደር።
ለሁሉም የሚበጅ የቤተሰብ ደንቦችን በማውጣት ዝምድናን ማጎልበትና መከባበር።
ህጻናት በጥሩ ሁኔታ አብረው ሲታዩ ማበረታታትና በማመስገን ማጠናከር።
አንድ ህጻን የራሱን ፍላጎት እንዲከተል ማድረግ።
ታዳጊ ህጻናት አብረው ለመጫወት ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድባቸው ግምት ውስጥ ማስገባት ይሆናል።
ከእያንዳንዱ ህጻን ጋር ወይም በጋራ አብሮ የተወሰነ ጊዜ ማሳለፍ።
ህጻናት ለሚያቀርቡት ክርክር ጊዜ በመስጠት መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ ታዲያ አለመስማማት ሲፈጠር ለመቆጣጠር አመቺ ይሆናል። ህጻናት ለአንድ ነገር መፍትሄ ለማግኘት የርስዎን እርዳታ ከፈለጉ መጠየቅ ነው። ህጻናት ለችግሩ መፍትሄ ማግኘት ካልቻሉ መሳተፍ። ማንንም አለመኮነን። መፍትሄ ለማግኘት መጣር።
ሌሎች ህጻናት ምን እንደሚሰማቸው እንዲያውቁ ማድረግ።
ሁሉም ነገር ለሌላ ሰው ማካፈል እንደማይቻል ማስረዳት።