እርስዎ ወላጅ እንደመሆንዎ ስለማወቅ

በተቻለን መጠን ሁላችንም በጣም ጥሩ ወላጅ ለመሆን እንፈልጋለን

እንደ ወላጅ መሆን ሁላችንም ስለ ወላጅነት ብዙ ሃሳቦችን ማፍለቅ እንጀምራለን። እንደ ወላጅ መጠን ለልጆቻችንና ለራሳችን የወደፊት ተስፋ ይኖረናል። አንዳንዴ ወላጅ በፈለግነው ትክክለኛ መንገድ ላይ ይደርሳል። ይሁን እንጂ አንዳንዴ ደግሞ ባልፈለግነው ሁኔታና እንዴት እንደተከሰተ በግልጽ ሳይገባን ሲቀር ለልጆቻችን ምላሽ በመስጠት ላይ እንቅፋት እንደሆነ ሊሰማን ይችላል።

ልክ እንደ ልጆቻችን የእኛም የሕይወት ልምድ አቀራረጽ ማንነታችንን ይገልጻል። በአካባቢያችን ባሉ ብዙ ምንጮች ማለት ወላጆች፣ ቤተሰብ፣ ጓደኞች የህጻን እንክብካቤ መስጫ፣ ትምህርት ቤቶች፣ ባለሙያዎችና የብዙሃን መገናኛ ያካተተ በመመርኮዝ ስለ ህጻንነትና ወላጅነት ያለንን ሃሳብ በስእል መግለጽ እንችላለን።

እንደ ወላጅ መሆን የምናውቀውን ነገር ብዙ ጊዜ እንደጋግማለን። ብዙ ጊዜ በልምድ ላይ የምናገኘው ነገር በሚገባ የምናውቀው ይሆናል። ከመጀመሪያ ቤተሰቦቻችን ጋር ስናድግ ያገኘናቸው ልምዶች ስለ ህጻናት፣ አሳዳጊና ቤተሰብ ለሚከሰተው የልምድና እምነት ጠቃሚ መሰረት እንደሚሆን ነው።

ካለን የተሻለ ግምት በአንጻጻራዊ ነገሮችን ስለማካሄድ ….

ሁሉም ወላጆች ከራሳቸው ግምት በአንጻሩ ህጻናት ያደርጋሉ ወይም ይናገራሉ የሚሉበት ጊዚያት እንዳሉ ነው።

‘በልጆች ላይ መጮህ አልፈልግም ነበር፤ ይሁን እንጂ የልብስ መቀለፊያየን በመገፍተራቸው የተነሳ በጣም ተበሳጨሁ ከዚያም እራሴን መቆጣጠርና ማቆም አልቻልኩም።’

በዚህን ጊዜ ወላጆች እራሳቸውን፣ ሚስት/ባላቸውና ለልጆቻቸው እንደሚያሳዝናቸው ነው።

ስሜቶች ሊጠፉ እንደሚችሉና በወቅቱ ግን ጥሩ ወላጆች ማግኘት ነው። እነዚህ ስሜቶች ከየት እንደመጡ ካወቅን ታዲያ ለልጆቻችን ምላሽ በምንሰጥበት ጊዜ በምን መልኩ ለመቀየር ያስችለናል።

ለልጅዎና ለርስዎ ስለማወቅ

ህጻናት እንደ ሁኔታው መለዋወጥ እንዳለባቸውና በእኛ ስሜትና ባህሪ ቂጥጥር ስር ስለመሆናቸው ይኮንኑናል። የጭንቀት መንፈስ ካለን፤ ከደከመን፣ ከተበሳጨን ወይም ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ሲኖረን ታዲያ ከሁኔታ ጋር ለሚለዋወጡ ነገሮች ምላሽ ለመስጠት ያለን ችሎታ ሊጠፋ ይችላል።

እንደ ወላጅ መሆን መጠን ያለብንን አነሳሽ ነገር ወይም የሚገፋፋን ምን እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል። ብዙ ጊዜ የልጆቻችን ስሜት ወይም ባህሪ ነእኛ ስሜትና ባህሪ ላይ ብስጭት ንዴትን ሊቀሰቅስ ቢችልም ታዲያ በርስዎና በልጁ መካከል ላለው ሁኔታ ጠቀሜታ እንደማይኖረው ነው። በሚገባ ምላሽ ለመስጠት ያመች ዘንድ የግል ፍላጎታችንና ስሜታችንን ህጻኑ ካለው ሁኔታ ጋር ለመለየት መሞከር ያስፈልጋል።

በራሳችን ጠለቅ ብለን በማየት ለምን እንዳሰብን፣ እንደተሰማንና ለማድረግ ባሳየነው ባህሪ ላይ በበለጠ አድራጎታችንን ልንረዳ እንችላለን። በራሳችን አጥልቀን በማየትና በማወቅ እንደ ወላጅ መጠን እንደ ሁኔታው ተለዋዋጭና ለመልመድም ያስችላል።

ስለ አሳዳጊ መሆን ሃሳብዎ ከየት ነው የመጣው?

ስለህጻናት አመጣጥ ግምትዎ ከየት ነው የመጣው?

የርስዎ የልጅነት ጊዜ ልምዶች በምን መንገድ ዛሬ ስለሚገኙበት የወላጅ ሁኔታ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል?

ስለ አሳዳጊነቴ የምወደው ምንድ ነው?

ስለ አሳዳጊነቴ ለመቀየር የምፈልገው ምንድ ነው?

ከወላጆች የፈለጉት ለየት ያለ ነገር፣ እንደ ወላጅ መጠን ልጄ ከእኔ የሚፈልገው ምንድ ነው?

ልጄ እያደገ ሲሄድ ያለኝን የአስተዳደግ አቀራረብ አቋም መቀየር የሚያስችለኝ ምን ማሰብ አለብኝ?