አባትም እናትም በስራ ላይ ሳሉ ልጅ ሰለማሳደግ

አባትና እናት ሁለቱም ወላጆች በስራ ላይ ሆነው ለቤተሰብና ለስራ ጊዜአቸውን ማመጣጠን አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። የቤተሠብና የልጆችን ፍላጎት ግምት ውስጥ በማሰገባት በጥንቃቄ ማሰብና ፕላን ማውጣት ጠቃሚ ነው። ይህም ከሥራ ብዛትና ከቤተሠብ አኗኗር ጋር በተገናኘ መልኩ የሚመጣን ጭንቀት ሊያስወግድ ይችላል።

ወላጆች ሥራ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ጥሩ መዋለህፃናት በጥንቃቄ መምረጥ በጣም ጠቃሚው ነው። ለትምህርት እድሜአቸው ያልደረሱ ልጆች ካሉ ለወላጅና ለልጆች የሚስማማ መዋለህፃናት መምረጥ በጣም ወሳኝ ነው። ለትምርህት የደረሱ ልጆች ካሉ ከትምህርት ሰዓት በፊትና በሁዋላ የሚቆዩበት ስፍራ ይፈልጉ ይሆናል። ብዙ አይነት ልጆች የሚቆ በትና እነክብካቤ የሚያገኙበት ስፍራ ያገኛሉ። በተለይም እድሜአቸው ለትምህርት ያልደረሱ ልጆች ከዘመዶቻቸው ጋር ፤ከግለሰቦች ጋር ቤትን በመሰለ አከባቢና በተለያዩ የመንከባከቢያ ማእከሎች መቆየት ይችላሉ።

አባትና እናት በጋራ ሆነው ለልጆቸቻው መዋለህፃናት ለመምረጥ መሞክር አላባቸው። ከመዋለህፃናት ወይም ከትምህርት ቤት ማን እንደሚያደርሳቸውና ማን እንደ ሚመልሳቸው መታሰብ አለበት። የስራው ጸባይ በተለያየ ጊዜ መውጣት ማን እንደሚያስችለው መነጋገርና ማን የሥራ ሰአቱን ልጆቹ በሚፈልጉት መልክ ማመቻቸት እንደሚችል መነጋገር ያስፈልጋል ። አንድ ወላጅ ብቻ ይህንን ማድረግ የሚችል ከሆነ የሥራ ውጥረቱን ለማገዝ ሌላው ወላጅ ምን መርዳት እንደሚችል መነጋገር ይገባል።

ሁለቱም ወላጆች በሚሠሩበት ጊዜ የታመሙ ልጆችን መንከባከብ ትልቅ ጭንቀት ሊያሰከትል ይችላል። ልጆች መታመማቸው የማይቀር ነው። አንድ ወይም ሁለት ከፍያሉ ጎልማሳ ሰዎች ምናልባትም ዘመድ ወይም የቤተሠቡ አባል ልጆቹ በሚታመሙበት ጊዜ እንዲንከባከቡ ተጠባበቂ ማኖር በጣም ጠቃሚ ነው።

ሁለቱም ወላጆች በሚሠሩበት ጊዜ እያንዳንዱ ወላጅ እኩል ልጆቹን መንከባከብና የቤትን ስራ እኩል መሥራት ያስፈልጋል። ሁለቱም ቤተሠቦች በጋራ ጊዜያቸውን በአንድላይ ማሳለፍ፣ በግልም፣ እነድቤተሠብም ጊዜን ማሳለፍ ያሰፈልጋል፡፤ልጆች ቤተሠቡ አባል የመሆናቸው ስሜት እንዲሰማቸውና ወላጆቻቸው መጠን በሌለው መልኩ እነደሚያፈቅሯቸው እንዲሰመቸው ያስፈልጋል።

ሁለቱም ወላጆች በሚሠሩበት ጊዜ የቤት ውስጥ ስራን መጋራት ጠቃሚ ነው።የቤት ውሰጥ የዘወትር ሥራ የአንድ ወላጅ (የአባት ውይም የእናት) ሃላፊነት ነው ብለን ከአሰብን ቅሬታን እያከማችን እንመጣለን። በእድሜአቸው ከፍ ያሉት ልጆች የቤትውስጥ ስራን ሊረዱ ይችላሉ፡ በአጠቃላይ ቅዳሜ ጠዋትን ለረጅም ጊዜ በመመደብ የቤት ስራን በመስራት የተቀረውን የሣምንቱን እረፈት ጊዜ ለቤተሠብና ለግል ጉዳዮች መጠቀም ይቻላል።

ሁለቱም ወላጆች በሚሠሩበት ቤተሰብ አንደኛው ወላጅ ልጆቹን በሚነከባከብበት ጊዜ እያንዳነዱ ወላጅ ለራሱ ጊዜ ይፈልጋል። ይህም እነርሱ በሚፈልጉበት ወይንም ሌላ እነቅስቃሴ ወይንም እረፍት በማድረግ ማሣለፍ ያሰችላል።

ሁለቱም ወላጆች በሚሠሩበት ጊዜ እንደባለትዳር አንድ ላይ የሚሆኑበት ጊዜ ማግኘት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ቤተሰቦች በዚህን ጊዜ ነው እራሳቸው ከልጆቹ ጋር ከመሆን ፋንታ ልጆቻቸውን የሚጠብቅላቸው ሰው እንደሚያሰፈለጋቸው የሚሰማቸው። ወላጆች አንድ ላይ በመሆን አርስ በርስ የሚደሰቱበትና የጎለማሳ ጉዳዮቸንና ድረጊቶችን የሚወያዩበት ጊዜ ያስፈልጋቸዋል።