ከወላጅ ጋር ለሚከሰት ጠብ መቆጣጠር

በዛሬው ቀን በቤተሰቦች ላይ የተለያዩ አስጨናቂ ነገሮች ስለሚደርሱ ታዲያ በወላጅነት ባለው ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር እንደሚችል ነው። አንዳንድ ጊዜ በአሳዳጊነት ያለው የሥራ ተግባር በወላጆች መካከል ውጥረትና ጠብ ሊፈጥር ይችላል። አንዳንድ አለመግባባት በዝምድናው ላይ ተቀባይነት የሌለውና ጤናማ አይሆንም። ይህንን ጠብ እንዴት ማስተናገድ እንደሚገባ ማወቁ ጠቃሚ ጉዳይ ይሆናል። አለመስማማትን ማስወገድ ሲባል ለጠቡ ዋና ምክንያት የሆኑትን ጉዳዮች ማስወገድና በተሻለ መልኩ መፍትሄ ለማግኘት መጣር ይሆናል።

ወላጆች በየቀኑ ለሚከሰቱት ጭቅጭቆች የአያያዝ ዘዴ በልጆቻቸው ላይ በጣም ጠቃሚ የሆነ ውጤት ይኖረዋል። ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያሳዩት ባህሪ ከህጻን አስተሳሰብና ደህንነት ጋር በጣም የተያያዘ ነው።

ወላጆች ተባብረው እንዴት እንደሚሠሩ ሲያሳዩ ከዚህ ህጻናት ይማራሉ

ወላጆች ደህና ሲሆኑና ያላቸው ዝምድና በጥሩ ሁኔታ የተጠበቀ ከሆነ የህጻንን ግንዛቤንና ከሌሎች ጋር ለሚኖራቸው ግንኙነት ይረዳል። ህጻናት ወላጆች ከቀን ወደ ቀን ከተጨቃጨቁና ልዩነታቸውን ገንቢ በሆነ መንገድ መፍትሄ ካገኙ ታዲያ ህጻናት ችግር ሲያጋጥም እንዴት መቋቋምና ማስተናገድ እንደሚችሉ ለመማር ይችላሉ። ይሁን እንጂ በወላጆች መካከል መፍትሄ ባላገኘ ተደጋጋሚ ጭቅጭቅ ሳቢያ ህጻናት በአንጻሩ በጣም እንደሚቸገሩ ነው።

ለህጻናት አንጻራዊ የሆነና ችግር ሊያመጣ በሚችል ጭቅጭቅ ላይ ማየት ወይም መስማት የለባቸውም። ህጻናት በቤት ውስጥ ስሜት በሚነካ ሁኔታ ላይ በጣም ቁጡ እንደሆኑና በቀላሉ ጭንቀት ያድርባቸዋል።

አንዳንድ ህጻናት ጠብ ሲፈጠር ከሌሎቹ በተሻለ ሁኔታ ይቋቋሙታል። ይህም ከህጻኑ የተፈጥሮ አመልና ለህጻኑ እርዳታ ሊሰጥ የሚችል ለምሳሌ ከአያት ወላጆች ጋር ጠቃሚ ግንኙነት ከመኖሩ ጋር የተያያዘ ይሆናል።

ጭቅጭቅ ለህጻናት አስጨናቂ ጎጂ ሊሆን ይችላል። በወላጆች መካከል የሚፈጠሩ ብዙዎቹ ጭቅጭቆች የተለያዩ የባህሪ፣ የማሕበራዊና የእድገት ችግሮችን በህጻናት ላይ ሊያስከትል ይችላል። ህጻናት ሊጨነቁ፣ ሊጓጉ፣ ሊቆጡ፣ ሊበሳጩ ወይም እምቢተኛ ሊያደርጋቸው ይችላል። የእንቅልፍ መረበሽ፣ ረጋ ብሎ በአንድ ሁኔታ ላለማተኮርና የመማር ችግር እንዲሁም ከእህት ወንድም ጋር በሚኖር ዝምድና ላይ ችግር ሊከሰትባቸው ይችላል።

ጭቅጭቅን ስለማስተዳደር

ከህጻናት ፊት ሆኖ አለመጣላት።

ህጻናት ወገናዊነትን ለመውሰድ ሲፈልጉ ጣልቃ እንዲገቡ አለማድረግ።

ባለቤትዎ እርስዎ ባሉት መንገድ ለመስማማት ልጅዎን እንደ “ማስገደጃ” አድርጎ አለመጠቀም።

ጠብ በሚከሰትበት ጊዜ ረጋ ባለ መንፈስ እንዴት ለልዩነቱ መፍትሄ ለማግኘት መወያየት ጥሩ አርአያ መሆን።

ለብስጭቱ ህጻናት እንደሆኑ አድርጎ ላለመኮነን ግልጽ ማድረግ።

ህጻናትን እንደሚወዷቸው በድጋሚ ማረጋገጥና ለችግሩ መፍትሄ እየፈለጉ መሆንዎን ማሳወቅ።

ለልጅዎ ለማዳመጥ ጊዜ መስጠትና ስለ ጠቡ ልጅዎ ያለበትን ስሜትና ጭንቀት ማመን።

በርስዎና በባለቤትዎ ያሉትን የሃሳብ ልዩነቶች ማክበር – ሁልጊዜ ላይስማሙ ይችላሉ።

ምንም እንኳን በነገሮች ላይ ካልተያያችሁ እንደ ወላጆች መሆን መጠን ለመተባበር ፈቃደኛ መሆን ይገባል።

የጠቡ ደረጃ በልጆችዎና ብትዳርዎ ላይ አንጻራዊ ችግር ካስከተለ የባለሙያ እርዳታ ያስፈልግዎታል።