እያንዳንዱ ህጻን የተለየ ነው
እንደ ወላጅ መጠን በልጆቻችን መካከል ያለው ሁኔታ ያለማቋረጥ ከሌሎች ጋር እናስተያያለን። ይህም ታላቅ የኩራት ምንጭ ሲሆን እንዲሁም በልጃችን ላይ የሆነ ስህተት ካለ የጭንቀት ምንጩ ሊሆን ስለሚችል ታዲያ እንደ ወላጆች መሆናችን የሆነ ስህተት እንዳደረግን ሊሰማን ይችላል።
እያንዳንዱ ህጻን ከሌላው የተለየ ነው። ህጻናት በተለያየ መንገድ ያድጋሉ፤ የተለያየ ግላዊ ሁኔታ፤ ተሰጥኦና ጥንካሬ ሲኖራቸው እንዲሁም የግላዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የተለያየ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
ሁሉም ህጻናት በራሳቸው እርምጃና መንገድ እንዲያድጉ ነው
ህጻናት በተለያዩ ደረጃዎች እንደሚያድጉና እንደሚሻሻሉ ነው። በእድገት ጉዟቸው ላይ ሊቀየር ሲችል፤ አብዛኞቹ ግን በተገመተው የእድገት ጎዞ ላይ እንደሚያልፉ ነው። ህጻናት በተለያዩ የድገት ደረጃ ጊዚያት ላይ ፈትለክ እንደሚሉና በአንዳንድ ደረጃዎች ደግሞ ቀስ ማለቱ የተለመደ ሁኔታ ነው። የልጅዎ እድገት ትንሽ ወደፊት ፈጠን ካለ ወይንም በተወሰነ እድሜ ገደብ ላይ ዝግመት ካለ፤ ይህ የተለመደ ጉዳይ ነው። በአብዛኛው ጊዜ ትክክለኛ የማሳደግ እንክብካቤና ማበረታቻ የሚያገኙ ህጻናት መጨረሻቸው የተሳካ ይሆናል።
ሁሉም ህጻናት የተለያየ ጥንካሬና በቀላሉ ተጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቹ በስፖርት ላይ ጥሩ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በሙዚቃ ይሆናል። አንዳንዶቹ በአካዳሚ ትምህርት በጣም ጎበዝ ሲሆኑ ሌሎቹ ግን ጎበዝ አይደሉም። አንዳንዶቹ በጣም ጭንቀታም ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በበለጠ ይዝናናሉ። አንዳንድ ህጻናት ጥሩ እንቅልፍ ሲተኙ ሌሎቹ ደግሞ ለዓመታት የሚሆን ማታ ማታ እንደማይተኙ ነው።
በትክክለኛ መስመር ላይ እንደሆኑ በራስዎ እምነት ስለማሳደር
ብዙ ወላጆች ‘ለአሳዳጊነት መብታቸው ታላቅ ተጽእኖ እየጨመረ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ በታላቅ ተጽእኖ ላይ ቢሆኑም ልጆቻቸውን ለማሳደግ ደህና እንደሆኑና ታዲያ ልጆቻቸው በትምህርት ቤት፣ በመዝናኛና በሥራ ቦታ ላይ የተሳካ እንዲሆን ይገምታሉ።
ብዙ ወላጆች እንደሚሉት አሳዳጊነት ለነሱ በተፈጥሮ የሚመጣ እንዳልሆነ ይሰማቸዋል።
ወላጆች ህጻናትን በሚያሳድጉበት ጊዜ ለእይንዳንዱ ልጅ ፍላጎት በጥሩ ሁኔታ ስለመሟላቱ ለማወቅ በራሳቸው እምነት አይኖራቸውም። ብዙ ወላጆች ስለአሳዳጊነት አቅርቦታቸው በሌሎች የሚፈረጅ መስሎ ይሰማቸዋል። ስለዚህ በእነዚህ ልምዶች ሳቢያ ወላጆች ለብቻቸው እንዲሆኑና ብዙዎች ወላጆች ተመሳሳይ በሆነ ተመኩሮ እንደማይጓዝ መስሎ ይታያቸዋል።
እነዚህ በሙሉ የተለመዱ ስሜቶችና ልምዶች ናቸው።
ለብቻዎ አይደሉም
የልጆቻችን ፍላጎትና ችሎታ በየጊዜው እያደገ በሚመጣበት ጊዜ የአሳዳጊነት ሥራ ተግባር ባለማቋረጥ እየተቀየረ ይሄዳል። ለወላጅ የሚሆን ዘዴና ‘ለሁሉም የሚስማማ እንድ ዓይነት መጠን እንደሌለ ነው። ለአንድ ህጻን የሠራው ለሌላው ህጻን ላይሠራው ይችላል። ህጻናት እድሚያቸው ሁለት ዓመት እያሉ የሠሩትን እድሚያቸው አራት ዓመት ሲሆን ላይሠሩት ይችላሉ።
ሁኔታዎችን በመስማማት መቀበልና ተለዋዋጭ መሆን ለአስፈላጊነት ቁልፍ መስራች አቋም ይሆናል።
በተወሰነ ጊዜ የወላጅነትን እምነት ማጣቱ የተለመደ ጉዳይ ነው። ከሌሎች ወላጆች፣ ጓደኞችና ቤተሰብ አባላት ጋር ያለዎትን ልምድ ማካፈል ነው። ስለዚህ እርስዎ ብቻዎን እንዳልሆኑ ያውቃሉ።
ልጅዎን ከማንም ሌላ ሰው በበለጠ እንደሚያውቁት እምነት ማሳደር ነው።
በመጨረሻም ልጅዎን ከሌሎች ጋር ከማወዳደር ማስወገዱ ጥሩ ነው።
ስለ ልጅዎ የሚያሳስብዎ ጉዳይ ካለ ወይም ስለ ወላጅነት በተመለከተ እርዳታ ከፈለጉ፤ ይህ የርስዎን ጥንካሬ የሚያሳይ እንጂ ድክመትን አይደለም።