በቅርብ ጊዜ እንደምወዳችሁ ስለመንገር

ወላጆቻችን ብዙጊዜ እንደሚሉን ህጻናት ምንጊዜም ከነርሱ ጋር እንደሆኑ ነው። ህጻናት እንደሚወደዱ ለማሳወቅ ሲፈልጉ ጥሩ ነገር ሲያደርጉ ብቻ ሳይሆን ግን እነሱ እንደሚወደዱ ማረጋገጥ ይገባል።

እያንዳንዱ ህጻን የራሱ ባህሪ ይኖረዋል።

ነብስወከፍ ህጻን የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪ ሲኖረው ልዩነቱን ዋጋ በመስጠት ማበረታታት ይገባል።

አንድ ቤተሰብ፣ ጓደኝነትና ማሕበራዊ ግንኙነት ለመፍጠር እያንዳንዱ ህጻን የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ህጻናት ስለራሳቸው ጥሩ ስሜት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፤

እራስን በማሞገስ ጠቀሜታ ያለው ሰው እንደሆንክ አድርገህ ማሰብ። ይህ በህጻናት ላይ ለወደፊት ሙሉ እምነትንና ተስፋ ያሳድርባቸዋል።

ህጻናት እራሳቸውን በማድነቅ ጠቃሚ እንደሆኑ ማሰብ እና ሕይወታቸውን ለመምራት እንደሚችሉ ማወቅ ያስፈልጋል። ህጻናት አዲስ ነገር ሲማሩ በበለጠ በራሳቸው መተማመን ይኖርባቸዋል።

ሕጻናት ጠቃሚ ለመሆናቸው በአገላለጽ ዘዴ ሁልጊዜ እንደምትወዳቸው ምንገር ነው።

አብሮ ጊዜ በማሳለፍ እንደምትወዳቸው በመግለጽ የሚሉትን ማዳመጥና ብዙ በማቀፍና ፈገግታ በመስጠት መግለጽ ይገባል።

አነስተኛም ቢሆን በሚያስገኙት ውጤት ላይ ማድነቅ። በሙከራ ለሚያስገኙት ውጤት አድናቆትን መስጠት ይሆናል።

ላስገኙት ጥሩ ውጤት ልዩ ማስታወሻ ማስቀመጥ። አንድ ነገር ሲያደርጉ እንዲያውቁት ማድረግ።

ስሕተት መፈጸም ችግር እንዳልሆነና ለመማር አንዱ ዘዴ እንደሆነ እንዲያውቁት ማድረግ።

እንዲጠናከሩ መርዳት።

ቤተሰብን በተመለከተ የነርሱን ሀሳብ መጠበቅ። ምን እንደሚያስቡ ካወቁ ለመንከባከብ መንገድ ይከፍታል።

የራሳቸውን ችግር እንዲፈቱ መርዳት።

በነርሱ ላይ እምነት እንዳለዎት ማሳየት። አቋምን ግልጽ ማድረግና አለመለዋወጥ።

ትክክለኛ ባልሆነ ባህሪ ላይ ምላሽ መስጠት ነገር ግን ልጅዎን አለመውቀስ።

ምክር መስጠት ልጅዎን ለመጉዳት ሳይሆን ለማስተማር መሆን ይኖርበታል።

“እናቴ እንደምትወደኝ አውቃለሁ ምክንያቱም እኔ የማደርገው ሁሉ ጥሩ ነው ብላ ስለምታስብ።”

Listen
Update Required To play the media you will need to either update your browser to a recent version, enable javascript or update your Flash plugin.