የህጻናት ፍርሃትና ከፍተኛ ጭንቀት

አብዛኛው ህጻናት በሆነ ደረጃ ፍርሃት ያድርባቸዋል። የተለመደ ፍርሃት እንደ ጨለማ፣ ከፍተኛ ጫጫታ ፣ ትላልቅ እንስሳት፣ መጥፋት፣ ትልቅ አስፈሪ ፍጡርና ለብቻ መተኛትን ያካተተ ይሆናል። አንዳንድ ህጻናት አንዳንድ ጊዜ ወላጆቻቸው ይታመማሉ ወይንም ይሞታሉ በሚል ስጋት በጣም እንደሚፈሩ ነው።

እንዲሁም በህጻናት ስሜታዊ እድገት ላይ ከሚፈጠሩት ሁኔታዎች ጭንቀት አንዱ አካል ነው። በህጻናት ከፍተኛ የፍርሃትና የጭንቀት መንፈስ ሊያሳድርባቸው ይችላል። በህጻናት ሕይወት ላይ ብዙ ለውጦች በሚመጣበት ጊዜ ፍርሃትን ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ፡ ህጻናት ወደ አዲስ ቤት ሲቀይሩ፣ በአዲስ ት/ቤት ውስት ሲጀምሩ፣ ወይም በአዲስ ሥራ ላይ ሲሳተፉ ጭንቀት ሊያድርባቸው ይችላል። በህጻናት ወይም በሚወዱት ላይ ምን እንደሚመጣ ያለመረዳት ጭንቀትን ሊያሳድርባቸው ይችላል።

የህጻናት ጭንቀት በተለያዩ ባህሪያት ሊታወቅ ሲችል ማለት እንደ ከወንድም፣ እህትና ጓደኛ ጋር በመጣላት፣ ያለምክንያት መቆጣት፣ እንቅልፍ ባለመተኛት መቸገር፣ ብዙ በማልቀስ፣ አጥብቆ በመያዝና በእንብይተኝነት ትቶ መሄድ ናቸው። የህጻናት ባህሪን መቀያየር ምክንያት በወቅቱ ለማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ከህጻናት ጋር አብሮ በመቆየት በነሱ ላይ ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ስለሚረዳዎ ታዲያ የሚያስፈራቸውን ነገር ለመለየት ይችላሉ።

በርስዎ ህጻን ላለ ፍርሃትና ጭንቀት ምላሽ ስለመስጠት

ህጻናት በሚፈሩበት ወይም በሚጨነቁበት ጊዜ አለመሳቅ። ምንም እንኳን ያስፈራቸው ነገር የማይረባ ወይም ምክንያት አልባ ቢሆንም ነገር ግን ለልጅዎ በጣም ከባድና እውነተኛ ሆኖ ይታዩታል። ስለዚህ ተስፋ ላለመቁረጥና ላለመበሳጨት መሞከር ይገባል።

ለልጅዎ ስለሚያስፈሩ ነገሮች ማዳመጥ። ሁኔታዎችን በማመን ልጅዎን ለመርዳት ፈቃደኛ እንደሆኑ ማሳወቅ ነው።

ህጻናት ካለባቸው ፍርሃት ለመላቀቅ ጊዜ መስጠት ነው። ሳምንታት፣ ወራት ወይም እስከ ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል።

ስለ ፍርሃትና ጭንቀት ከህጻናት ጋር መነጋገሩ ስሜታቸውን ያረጋጋል። በልጅዎ ላይ ያለውን ጭንቀት በማረጋጋት ለመርዳት በቀላልና ረጋ ብሎ በብልሃት ገለጻ መስጠት ይሆናል።

ለርስዎ ባሳሰቡት ነገሮች ላይ ለመነጋገርና እነዚህን እንዴት አድርጎ ማስወገድ እንደሚቻል ለልጅዎ ማነጋገር ነው።

የሚያስፈራ ነገር አለመኖሩን ለህጻናት ከመናገር መወገድ ነው። ህጻናት እንዴት እንደተስማማቸው አለማወቅን በዚህ መልእክት ላይ ማስተላለፍ ይቻላል።

ህጻናት ስለሁኔታው እንዲያስቡ በማድረግ ጭንቀታቸውን ሊያቃልል ይችላል። ለምሳሌ፡ ልጅዎ በጨለማ ወይም በማታ የሚፈራ ከሆነ ታዲያ አሻንጉሊት እንደ መከላከያ በመጠቀም የመኝታ ጊዜ ስለመሆኑ መስምማማትና በዚህ አሠራር ለመቀጠል ክልጅች ጋር በጨለማ ብርሃን ማስገኛ እንዳለ መነጋገር ነው።

ብዙጊዜ ህጻናት ስለ ጭንቀት ገለጻ ማድረግ አይችሉም። ስላለባቸው ፍርሃትና ጭንቀት ለመናገር ሊከብዳቸው ይችላል። በህጻናት ላይ ያለን ፍርሃት በጨዋታ መልክ እንዲቆጣጠሩት መርዳት ነው። ለምሳሌ፡ ስለ ሀኪሞች መጫወቱ ህጻናት ወደ ሀኪም ሊሄዱ የሚያሳድርባቸውን ፍርሃት ለማስወገድ ሊረዳ ይችላል።

ህጻናት በተለቪዥን ላይ የሚያዩትን በመቆጣጠር ፍርሃትን መቀነስ ይቻላል። ሊያስጨንቃቸው በሚችል ተገቢ ባልሆነ ቆሳቁሶች ላይ ህጻናትን ማራቅ ይገባል።

እርስዎ በሚያውቁት ሁኔታና ለህጻናት ጭንቀት በማይፈጥር ነገር ላይ ለመውሰድ መዘጋጀት ነው። ህጻናት የሚጨነቁ ከሆነ ታዲያ በሁኔታው ላይ ማን እንደሚኖር፣ ምን እንደሚደረግና የማን ህጻን መሄድ እንደሚችል ማነጋገሩ ጥሩ ነው። ለምሳሌ፡ በአዲስ ትምህርት ቤት ላይ ሲጀምሩ፣ ብዙጊዜ ት/ቤት እስኪጀምር የመጀመሪያ ቀን ህጻኑን መውሰድ፣ ቅዳሜና እሁድ በመጫወቻ ሜዳ ላይ አብሮ ማሳለፍ፣ የትምህርት ክፍል መስጫው፣ ሽንት ቤቱ የት እንዳለና ከትምህርት በኋላ የት እንደሚገናኙ ቦታውን ማሳየት ይሆናል።

በህጻናት ሁኔታ ላይ አንዳንድ የመቆጣጠር ስሜት ሲያድርባቸው ታዲያ ለሚያድርባቸው ፍርሃት ይቀንሳል። ህጻናት ስለሚኖራቸው ፍርሃት ለመወጣት በጣም እንዲጥሩ ጫና አታድርጉባቸው። ስለሚኖራቸው ፍርሃት እንዳይሰማቸው መርዳት ነው። ለምሳሌ፡ ልጅዎ በትላልቅ ውሻዎች የሚፈራ ከሆነ ደህንነቱ በተጠበቀና በተያዘ የውሻ ስእሎችን በማሳየት፣ ከውሻ አሻንጉሊቶች ጋር በማጫወት፣ በቤት እንስሳት በሚሸጥበት ሱቅ ላይ ውሾችን ማሳየት እና ዝግጁ በሚሆንበት ጊዜ ትንሽና ለማዳ የሆነ ውሻ እንዲያሳድጉ ማበረታታት ይሆናል።

ህጻናት ስለሚያደርጉት የፍርሃትና ጭንቀት ቁጥጥር ማድነቅና ማበረታታት ይሆናል።

እርስዎ አስፈራሪ ወይም አስጨናቂ ስለመሆንዎ ለህጻናት አለማሳወቅ ምክንያቱም ይህ ያለባቸውን ፍርሃት ሊያባብስ ስለሚችል ነው። አንዳንዴ የርስዎ ጭንቀት ክህጻኑ የበለጠ ሊሆን ይችላል። ከርስዎ ብስጭት ስሜት ላይ ህጻናት በቀላሉ ሊወስዱት ይችላሉ። ታዲያ የራሳችንን ጭንቀት እንዴት መቆጣጠር እንደምንችል ማሰቡ ጥሩ ነው።

የባለሙያ ምክር መቸ እንደሚያስፈልግ

መበሳጨት በህጻናት ላይ በጣም የተለመደ ስለሆነ ታዲያ ጤናማ በሆነው እድገታቸው ላይ በጭንቀት መንፈስ ችግር ሲጀምር ወላጆች የባለሙያ ምክር ማግኘት አለባቸው። የልጅዎ የፍርሃትና ጭንቀት በመደበኛው የእለት ተእለት ኑሯቸው ላይ ጣልቃ በመግባት ከወራት በኋላ ከመሻሻል ፈንታ እየተባባሰ ከመጣ ከአጠቃላይ ሐኪምዎ/GP፣ ከህጻናት ሐኪም ወይም ከት.ቤት መማክርት ምክር ያስፈልግዎታል።