የልጅዎን ስሜታዊ እድገት ስለመረዳት

ስለ ስሜታዊ መሻሻል እድገት በምንነጋገርበት ጊዜ፣ የህጽናትን የችሎታ እድገት ለመጥቀስ ሲሆን፡

  • የነሱን ስሜት ማወቅና ለመለየት
  • የሌሎችን ስሜት ለመረዳትና በትክክል ለማንበብ
  • ስሜታቸውን ለመቆጣጠር
  • ያላቸውን ባህሪ ለማስተካከል
  • ለሌሎች የማፅናናት ስሜት ማዳበርና
  • ከጓደኞች፣ ቤተሰባና ከሌሎች ጋር ጥሩ ዝምድና መያዝና ማዳበር ይሆናል።

ህጻናት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ስሜቶችን ለማወቅና ችሎታን በፍጥነት በማዳበርና የተለያዩ ስሜቶችን ለመቋቋም ችሎታ ማዳበር ይሆናል።

ስሜቶችን ስለመቆጣጠር

ህጻናት የሚሰማቸውን የመቆጣጠርና የማስተካከል ችሎታ በእድገታቸው ላይ ወሳኙ ክፍል ሲሆን የዚህ ምንጩ ብዙጊዜ የወላጆች ሥራ ይሆናል።

ህጻናት ሰሜታቸውን እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ ካለ ችሎታ ጋር ሕይወት አይጀምሩም። በከባድ ስሜት በቀላሉ ሲጎዱ ታዲያ በቀላሉ ሊበርዱ አይችሉም። ህጻናትና ታዳጊዎች ይህንን ለመቆጣጠር የወላጆች እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

ህጻናት ማድረግ በሚፈልጉት ነገርና ማድረግ በሚችሉት መካከል ከፍተኛ ልዩነት ስለሚኖር ብዙጊዜ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያድርባቸዋል። ይህም ብዙጊዜ ያለምክንያት የቁጣ መንፈስ ያሳድርባቸዋል።

ባህሪና ስሜት በጣም የተያያዙ ናቸው። ስሜትን በደንብ ካልተቆጣጠሩ የህጻናት አስተሳሰብ ችሎታ ሊበላሽ ይችላል። በመጨረሻም ህጻናት ብዙጊዜ ሳያስቡ በስሜታቸው ይወስናሉ።

ህጻናት ት/ቤት በሚጀምሩበት ጊዜ በበለጠ ስሜታቸውን በመቆጣጠር ስለሌሎች ስሜት ማወቅ ይጀምራሉ። የሚያስቡትንና የሚሰማቸውን በበለጠ በማቀናጀት ስሜታቸውን ለመግለጽ ቃላቶች ይጠቀማሉ። ይህም በሚሰማቸው መንገድ ላይ በበለጠ ለመቀየርና ለማስተካከል ይስችላቸዋል። ህጻናት ስሜታቸውን ለመቀየርና ለመላመድ እንዲችሉ ማለት በበለጠ የተስፋ መቁረጥ ስሜትን መቆጣጠር ያስችላል፤ ይህም ነገሮችን በመተው እራሳቸው ረጋ እንዲሉ ያስችላል።

ለህጻናት ስሜት ግንኙነቶች ጠቃሚ ናቸው

በወላጆቻቸውና በህጻናት መካከል ያለው የግንኙነት አይነት በህጻናት ስሜታዊ እድገቶች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ይኖረዋል። ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ተባብሮ የመሥራቱ ጉዳይ በልጆች ስሜታዊ እድገት አካሄድ ላይ ብዙ የሚደረጉ ዘዴዎች እንዳሉ ነው።

የህጻናት ቤተሰብ አባል እንዴት አድርገው ስሜታቸውን ሲገልጹና ሲቆጣጠሩ በመከታተል ታዲያ ልጆች ስሜታቸውን ለመቆጣጠር ከዚሁ ይማራሉ። ወላጆች በከባድ ስሜት ላይ በምን መልኩ ምላሽ መስጠት እንዳለበት ወላጆች ከፍተኛ የአርአያነት ሚና ይጫወታሉ።

ህጻናት ስሜታቸውን በመቆጣጠር ላይ እርዳታና ልምምድ ያስፈልጋቸዋል።