ከህፃን ጋር መግባባት መቻላችንን መረዳት

አዲስ የተወለደን ህፃን ወደ ቤት በሚመጣበት ጊዜ ወላጆችም ሆን ህጻኑ የመደሰትና የፍርሀት ስሜት ሊኖራቸው ይችላል። አዲስ የተወለደ ህፃንን በምንከባከብበት ጊዜ ዋናው ትኩረት መስጠት የሚገባን የህፃኑ ፍላጎት መሟሏቱን እርግጠኛ መሆን አለብን።

አዲስ የተወለዱ ህጻናት የሚፈልጓቸው መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች፤ህጻናት ይርባቸዋል፤ ይደክማቸዋል፡ አለመመቸት ናቸው።

ህፃኑ የ አለመመቸት ስሜት እንዲኖረው ከሚያደርጉት ነገሮች ጢቂቶቹን እነዝህን የጨምራሉ፡

  • በጣም ሲሞቃቸው ወይም በጣም ሲቀዘቅዛቸው
  • የሽንት ጨርቅ እነዲለወጥ ሲፈልጉ
  • ህመም ሲኖራቸውው (የጆሮ ህመም ፡የሆድ ህምም ፣ ከፍ ላሉ ህፃናት የጥርስ መታመምን ሊጨምር ይችላል)
  • በሚፈሩበት ጊዜ፡ ብቸኝነት ሲሰማቸው ወይም ሲሰለቹ
  • ጤነኛ ባልሆኑበት ጊዜ ( ምናልባት ከፍተኛ ትኩሳት)።

ህፃናቶች የቤተሠባቸውን ትኩረት ለማግኘትና ስለሚፈልጉት ነገር ከወላጆቻቸው ጋር ብዙ መግባቢያ መንገድ አላቸው። ወላጆች ከጊዜ በሓላ እነዚህ ምልክቶች ምን እንደሚያመለክቱና እነዴት ምላሸ መስጠት እንዳለባቸው ይማራሉ። መጀመሪያ ላይ እነዚህን ምልክቶች አለመረዳት ወይንም በተሣሣተ መልክ መተርጎም በቀላሉ መሳሳት ይቻላል። ህጻናቱ የሚሰጥቱን መልእክት ተረድቶ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ግዜ ይወሰዳል።

ህጻናት ለምን ያለቅሣሉ

ህጻናት ትኩረት ለማግኘት የሚጠቀሙበት ዋናው መልእክት ማልቀስ ነው። ህጻናት የተለያየ ነገር ሲፈልጉ የተለያየ ዓይነት ለቅሶ እንሚያለቅሱ በመለየት ወላጆች ቶሎ ይማራሉ። ሕጻናት የሚያለቅሱት አንድ ነገር ሲፈልጉ ብቻ ነው።

ህፃናቶች ወላጆቻቸውን “ለማበሣጨት” ወይንም “ወላጆቻቸውን ለማግኘት” ሲሉ አያለቅሱም። ህፃናት ሰሜት አላቸው ማሰብ ፤የሚመጣውን ቀድሞ መገመት ወይንም ነገሮችን አዙሮ ማየት አይችሉም።የእነሱ ለቅሶ ሌላው ሰው ላይ ምን ተፅእኖ እነደሚያሳድር አያውቁም። እነርሱ የሚያቁት አንድ ነገር መፈለጋቸውን ነው ይህንንም ፍላጎታቸውን ለመግለጽ ብቸኛው መንገድ በማልቀስ ነው። ህፃን ለመኖር ወይም የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት ያለቅሣል ስለዚህ ወላጅ ለዚህ ምልክታቸው ምላሽ መስጠት አለበት።

ሰለህጻን ልጃች ብዙ እያወቅን በሄድን ቁጥር ህጻናት የሚግባቡበት በዙ መነገዶች እንዳሉ እንገነዘባለን።

የህፃናንን ፊት በመመልከት ብዙ መግባቢያ መንገድ እንዳላቸው መረዳት ይቻላል። ወላጆች የህጻናትን ፊት በመመልከት ምን እንደሚፈልጉ አስቀድሞ በመገመት ህጻኑ የሚፈልገውን ማደረግ መቻል አለባቸው። የህፃናት ፊት በዙ ነገረን ይገልጻል። ካፍንጫቸው በላይ መሥመር በማሳየት የመጨነቅ ስሜታቸውን ያሳያሉ ፤ ይህም አንዳንድ ህፃናት ቶሎ የሽንት ጨርቅ እንዲለወጥ መፈለጋቸውን የሚጠቁም የመጀመሪያ ምልክት ሊሆን ይችላል።የህፃናት አፍም በጣም ስሜትን አሳዪና ህፃናት ከነፈራቸውን ሊያጨማድዱና ምላሳቸውን ለመግባቢያ ይጠቀማሉ።

ህፀናት እንደ ፊታቸው ሁሉ እጃቸውንም ጭምር አንድ ነገር መፈለጋቸውን ለመጠቆም ይጠቀማሉ ።ወላጆች ህፃናት ጡጫቸውን ሲጨብጡ የአለመመቸት ወይንም መራባቸውን ለመግለጽ የሚሰጡት ምልክት መሆኑን ይማራሉ።ህፃናት መላው ሠውነታቸውን የሚፈልጉትን ነገር ለወላጆቻቸው አስቀድመው ለማሰጠንቀቅ ይጠቀማሉ ብዙ ጊዜም ጀርባቸውን በማዞርና እግራቸውን በመምታት የሆነ ነገር መፈለጋቸውን ይጠቁማሉ።

ከህፃናት ጋር መግባባት

ህፃናት ከወላጆቻቸው ጋር እንደሚግባቡ ሁሉ ወላጆችም ከእነርሱ ጋር መግባበት ያስፈልጋቸዋል። የወላጆች ለህፃናት ማውራት፤ መሳቅና ማነበብ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ የምርምር ውጤት ያስገነዝባል። በመናገር ምንም መመለስ በማይችሉበት ጊዜ ወላጆች ህፃናትን ሲያናግሩና መጽሃፍ ሲያነቡላቸው ትንሽ የሞኝነት ሰሜት ይሰማቸዋል።ሆኖም ህፃናት ምላሽ ይሰጣሉ ወላጆች ሕጻናት ምን እነደሚፈልጉ ለመግለጽ የሚሰጡት ህጻናት የሚፈልጉትን ነገር ለመግለጸ የሚሰጡትን ምልክት አንደተማሩ። ህጻናትም መገባባት በሚሞክሩበት ጊዜ ምላሽ በመስጠት መግባባት ይሞክራሉ።

ህጻናት የሚያምሩና ውብ የሆኑ ነገሮችን በማሳየት ማነቃቃትን ይወዳሉ።መደሰታቸውንም በፊታቸውና ከሰውነታቸው እንቅስቃሴ በመግለጽ ይግባባሉ።ይህ የመግባቢያ ምልክት በወላጅና በህፃን መካከል መግባባት እነደተጀመረ የሚገለጸና የህም የመንከባከብና፤ የፍቅር ግንኙነት ህፃኑንና ወላጁን ሁለቱንም የሚደሱበት ሊሆን ይችላል።

መዳሰስ በወላጅና በህፃን መሃል ጠቃሚ የመግባቢያ ምልክት ነው። ወላጆች ህፀናታን በማሽት በዚህም ወቅት በሰውነታቸው አገላለጽ የሚሰጡትን ሁኔታ በመረዳት ህፃናቱ ምን እንደሚፈለጉና እንደማይፈልጉ ይማራሉ። መነከባከብ ማፍቀር በመዳሰስ ማለትም በማጫወትና እና በማቀፍ እንዲሁም በብዙ የተለያዩ መንገድ ህፃኑን መታቀፍ በተለይም ለህጻኑ ምቾት ለመስጠት ጠቃሚ መግባቢያ መንገድ ሲሆን በወላጅን በህፃኑ መካከል ያለውን የፍቅር ግኑኝነት ያዳብራል።