በልጅዎ ማሕበራዊ እድገት ላይ ስለመርዳት
ህጻናት ስለ ዓለማቸው ያለማቋረጥ ይማራሉ እንዲሁም ከሌሎች ጋር አብሮ እንዴት እንደሚኖር ይማራሉ። አንድ ህጻን ሌሎች እንዲያስተምሩት የማነሳሳት ፍላጎት ሲኖረው ታዲያ ህጻኑ አዲስ ነገሮችን ለመሞከር እምነት ያሳድርበታል።
የህጻናት ማሕበራዊ እድገት ካላቸው ስሜታዊ እድገት ጋር በቅርብ የተዛመደ ይሆናል። ህጻናት ስሜታቸውን ማለት እንደ ንዴት ወይም የመደነቅ ስሜት መቆጣጠር የሚችሉ ህጻናት ታዲያ ብዙ ጊዜ አወንታዊ በሆነ መንፈስ ከሌሎች ህጻናት ጋር እንደሚጫወቱና ችግርም በሚፈጠርበት ጊዜ ከሌሎች ህጻናት ጋር እንደሚወያዩ ነው። በተመሳሳይ የሌሎችን ስሜት የተረዱ ህጻናት ታዲያ በሚጫወቱበት ጊዜ የሌሎችን ፍላጎት በበለጠ ለማስተናገድ ይችላሉ።
እንደ ወላጅ መጠን ከልጅዎ ጋር እና በልጅዎና በሌሎቹ መካከል ግንኙነት እንዲፈጠር እርስዎ በጣም ጠቃሚ ሚና ይጫወታሉ። ለእነሱና ለሌሎች ከሚያሳዩት የአቀራረብ ዘዴዎች በመነሳት ህጻናት ስለ ዝምድናና አቀራረብ ይማራሉ።
ሁሉም ህጻናት በተለያየ የማሕበራዊ እድገት ደረጃዎች ይጓዛሉ። አብዛኛውን ጊዜ ህጻናት የማሕበራዊ ችሎትን በጨዋታና በውድድር በኩል ያዳብራሉ። የህጻናት ጨዋታ እንዴት ከእድሜ ጋር እንደሚቀየር። ህጻናት በሚያድጉበት ጊዜ ከሌሎች ህጻናት ጋር ለመጫወት ለብቻቸው እንደሚሄዱና በመጨረሻም ከሌሎች ህጻናት ጋር ተባብረው በጋራ ይጫወታሉ።
ልጅዎን ስለማወቅ
በተለያየ እድሜ ላሉ፣ ከተለያየ ሃገር ለመጡና የተለያየ ግላዊ ልምድ ያላቸው ህጻናት በማሕበራዊ ችሎታ እድገት ላይ የተለያየ ችግር ያጋጥማቸዋል። አንዳንድ ህጻናት በቀላሉ ጓደኞች ማፍራት ሲችሉ ለአንዳንዶቹ ደግሞ ከበድ ይላል። አንዳንድ ህጻናት አይነ አፋር ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ተግባቢ ናቸው። ህጻናት አንዳንድ ማሕበራዊ ችሎታን ለማዳበር ምንም ችግር አይኖርባቸውም ነገር ግን ሌሎቹ ችግር አለባቸው።
ልጅዎ በተለያየ ማሕበራዊ ሁኔታዎች ላይ ሲሳተፍ ማስተዋል። እንዴት እነደያዙት ማሳወቅ። በተለያዩ ቦታዎች ላይ ለመላመድ ልዩነት አላቸውን? በራሳቸው መተማመን ይጎድላቸዋልን? ተሳትፎ እንዲያደርጉ እርዳታ ያስፈልጋቸዋልን? በቀላሉ ማድረግ የሚችሉት ምንድ ናቸው? ለማድረግ በበለጠ የሚያስቸግሩ ነገሮች ካሉ ምንድ ናቸው?
ህጻናት ለመራመድና ለመናገር እንደሚማሩት ሁሉ ታዲያ የህጻናት ማሕበራዊ ችሎታ ለመሻሻል ድጋፍ፣ ልምድና ሁኔታዎችን በድጋሚ መስራት እንደሚያስፈልግ ነው።
ልጅዎን ለመርዳት መንገዶች
በቤት ውስጥ ርህራሄነትና ደግነትና የተሞላበት አካባቢ መፍጠር። እንዲያካፍሉ በማበረታታ የሌሎችን ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ማድረግ።
ለልጅዎ የሚፈልጉትን ማሕበራዊ ባህሪ እንዲይዝ እርስዎ ምሳሌ መሆን። እንዲሁም ትላልቅ እህትና ወንድሞች ለታናሽ ወንድምና እህቶች ጠቃሚ የአርአያ መሆን ድርሻ ሊኖራቸው ይችላል።
ህጻናት በየቀኑ ለሚከሰት አሰልቺ ሥራ ለርዳታ መጠየቅና እንደፈለግጉ እርዳታ መስጠት ይሆናል።
በልጅዎና በሌሎች መካከል ተገቢ የሆኑ ዝምድናዎች እንዲፈጠሩ ማበረታታት - ለሁለቱም ማለት ለጎልማሶችና ህጻናት።
ህጻናት ስለራሳቸው አወንታዊ የሆነ ስሜት እንዲኖራቸው መርዳት። አወንታዊ በሆነ እራስን ማድነቅ ለጤናማ የሆነ ማሕበራዊ መሻሻል ወሳኝ ነው።
ህጻናት ስለሚኖራቸው ስሜትና ስለሌሎች ሰሜት እንዲያውቁ መርዳት ይሆናል።
ልጅዎ እንዴት በቡድን እንደሚሳተፍ፣ ተራ እንደሚጠብቅና ደንቦችን ለመከተል ችሎታ ማዳበር እንዳለበት መርዳት።
ስለ ተካፍሎ መጠቀም በተገቢው ግምት ውስጥ ማስገባት። ህጻን በጋራ ለመጫወት አንዳንድ አሻንጉሊቶች በበለጠ ሊያስቸግሩ ይችላሉ፣ ለምሳሌ፡ ለሚወዱት አሻንጉሉት። ታዲያ ልጅዎ ከሌሎች ጓደኞች ጋር በሚጫወቱበት ጊዜ እነዚህን ነገሮች አርቆ ማስቀመጥ ይሆናል።
ህጻናት አብረው ሊጫወቱ የሚችሉበትን በብዛት እድሉን ማቅረብ ይሆናል።
ልጅዎ ብዙ ጊዜ ለሚያሳልፍበትና ለጨዋታ ቀናት በሚቀናጅበት ለልጅዎ የቅድመ ት/ቤት ወይንም ት/ቤት መጠየቅ ነው።
ለታዳጊ ህጻናት የጨዋታ ቀናትን አጭር፣ ቀላልና አስቂ እንዲሆን ማድረግ። በጣም ታዳጊ ለሆኑ ህጻናት ስለጭዋታ እንቅስቃሴ መዋቅር ማስተዋወቅ ይሆናል። ለህጻናት የተወሰነውን ጊዜ ቀስበቀስ በማራዘም ታዲያ የተሳታፊ ህጻናት ቁጥርን መጨመር፣ ልጅዎ እያደገ ሲሄድ በቦታው የተቀመጠውን መዋቅር መጠን በመቀነስ ታዲያ ህጻናት እነዚህን ሁኔታዎች ለማካሄድ ችሎታ ሲያዳብሩ ማየት ይችላሉ።