በራስ ለመመራት ስለማነሳሳት
ህጻናት በሚያድጉበት ጊዜ የወላጆችንና የጓደኞችን ድጋፍ በትክክል ይጠቀሙ ዘንድ ታዲያ ህጻን በራሱ እንዲመራ፣ በራሱ አነቃቂነት መሥራት እንዲችል ማድረጉ የወላጅነት ዋና ተግባር ይሆናል። ልጅዎ ጤናማ የሆነ በራስ ችሎ የመመራት ስሜት እንዲያድርበት ለማድረግ መርዳት ይችላሉ። በራስ መተማመን በልጅዎ እድገት ላይ ጠቃሚ የሆነ ጉዳይ ነው። ህጻናት ከሁለት ዓመት እድሜ ጀምሮ ብዙ የራስ መተማመን መንፈስ ይኖራቸዋል። ታዲያ ከዚህ እድሜ ጀምሮ ህጻናት ስለኑሯቸው ቀላል ምርጫዎችን ማድረግ ይችሉ ዘንድ ማበረታታት ይገባዎታል።
ከልጅዎ የሚጠብቁት የራስ መተማመን ደረጃ ከእድሜያቸውና ችሎታቸው ጋር የተመሳሳለና ምቹ መሆን ሲገባው ነገር ግን እንደሁኔታው ሊለያይ ይችላል። ህጻናት በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ በበለጠ የራስ መተማመን ሊኖራቸው ይችላል።
ህጻናት ለማድረግ የሚችሉትን ነገሮች ለማካሄድ ሥራ ለሚበዛባቸው ወላጆች የተለመደ ወጥመድ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ህጻናት በሚያድጉበት ጊዜ ከእድሜ ጋር ተመጣጣኝ የሆኑትን ሥራዎች በራሳቸው ሙሉ እምነትና መተማመን ለማካሄድ ከወላጆች እርዳታ ለማግኘት በመጀመሪያ ብዙ ጊዜ ሊወስድባቸው ይችላል።
በትክክለኛ የራስ መተማመን ለማበረታቻ መንገዶች
እርስዎ ከፈቀዱትና ባዘጋጁት የተለያዩ አማራጭ ተግባራት ላይ ልጅዎ ቀላል የሆኑ ምርጫዎች እንዲያደርግ እድሉን መስጠት። ለምሳሌ፡ ልጆችዎ በየቀኑ ለሚለብሱት ልብሶች፣ ምንም እንኳን የተወሰነ የህብረ ቀለም ምርጫ ቢኖርም በራሳቸው ምርጫ እንዲሆን መፍቀድ ነው።
ህጻናት ስህተት እስኪያደርጉ ማየትና ከስህተታቸው እንዲማሩ መርዳት ነው።
ህጻናት በቤት ውስጥ ባለ ሥራ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ማለት እንደ ቫኩም ጽዳት፣ አቧራ ማራገፍና አልጋ ማንጠፍ ይሆናል።
የሃላፊነት እድገታቸውን በሰንጠረዥ መመዝገብ ስለዚህ ህጻናት የቤት ውስጥ ሥራዎችን በሚያጠናቅቁበት ጊዜ የደረሱበትን ደረጃ ማስቀመጥ ይችላሉ።
ህጻናት ስለሚያስቡትና ባላቸው ሃሳብ ላይ እርስዎ ደስተኛ እንደሆኑ ያሳውቋቸው። ከእነሱ ጋር በሚያደርጓቸው ነገሮች ላይ የእንሱን አስተያየት መጠየቅ ነው።
በተቻለ መጠን የልጅዎን ውሳኔዎች ማክበር ነው።
ህጻናት በሚወስዱት ምርጫዎች ላይ ያለውን ችግር እንዲረዳቸው መርዳት።
ስለችግር መፍትሄ ማግኘት ችሎታ ህጻናትን ማስተማር – በራሳቸው ስለ ችግር መፍትሄ ለማግኘት ምን ማድረግ እንደሚገባ እንዲያስቡ ማበረታታት እንጂ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አለመንገር ነው።
ለልጅዎ ሁኔታው አስቸጋሪ ከሆነ አወንታዊ የሆነ እርዳታ ማቅረብ ነው።
የፈለገው ውጤት ቢመጣም ህጻናት በራሳቸው አነሳሽነት እንዲሠሩ ማበረታታትና ማድነቅ ይገባል።
ከእድሜ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ አሻንጉሊት በማቅረብ ታዲያ ህጻናት ለአጭር ጊዜ በራሳቸው ለመጫወት መማር ይችላሉ።
ህጻናት የተጫወቱበትን አሻንጉሊቶች በራሳቸው ለማሰባሰብ ሃልፊነቱን እንዲወስዱ መርዳት ነው።
በእድሜ ተለቅ ላሉ ህጻናት ስለ ሰዓት አጠቃቀም በማስተማር ታዲያ እርስዎ ከሚሰጡት አንዳንድ መመሪያ ጋር እንዲያገናዝቡ ማድረግ ይሆናል። ለምሳሌ፡ “ለመጫወት ወደ ጎረቤት መሄድ ትችላለህ፣ ነገር ግን በሰዓት 4:30 ወደ ቤት እንድትመጣ እፈልጋለሁ”።
ህጻናት ከታለመው ግብ እንዲደርሱ መርዳትና እነዚህን ተግባራዊ ለማድረግ አብሮ መሥራት ይሆናል።