ስለመጀምሪያ ዓመታት
በህጻን ሕይወት ላይ እነዚህ የመጀምሪያ ዓመታት ለምድ ነው አስፈላጊ የሆኑት?
ህጻናት ማጫወት የወላጆች ሥራ ይሆናል
ህጻናት ከሚፈልጉት ነገር ጨዋታ አንደኛው ጠቃሚ ነገር ነው። ከልብ ከተጫወቱ ያስቃል።
ስለዚህ ህጻናት በአብዛኛው ጊዜ ሊማሩ የሚችሉት በጨዋታ መልክ ይሆናል።
ለህጻናት አእምሮ እድገት የወላጅነት ጠቀሜታ
ለሰው ዘር የአእምሮ እድገት ጊዜ ይወስዳል። ህጻን ሲወለድ ለሕይወት ዋና ጠቃሚ የሆኑ አሠራሮች በአንጎል በኩል ይደራጃሉ – ይህም መተንፈስ፣ የልብ ትርታ አለመቀያየር፣ መጥባት፣ መተኛትን ያካትታል። ሌላው የአንጎል አሠራር ለመዳበር አመታት ይወስዳል።
የልጅዎን ስሜታዊ እድገት ስለመረዳት
በልጅዎ ማሕበራዊ እድገት ላይ ስለመርዳት
ህጻናት ስለ ዓለማቸው ያለማቋረጥ ይማራሉ እንዲሁም ከሌሎች ጋር አብሮ እንዴት እንደሚኖር ይማራሉ። አንድ ህጻን ሌሎች እንዲያስተምሩት የማነሳሳት ፍላጎት ሲኖረው ታዲያ ህጻኑ አዲስ ነገሮችን ለመሞከር እምነት ያሳድርበታል።
በራስ ለመመራት ስለማነሳሳት
ህጻናት በሚያድጉበት ጊዜ የወላጆችንና የጓደኞችን ድጋፍ በትክክል ይጠቀሙ ዘንድ ታዲያ ህጻን በራሱ እንዲመራ፣ በራሱ አነቃቂነት መሥራት እንዲችል ማድረጉ የወላጅነት ዋና ተግባር ይሆናል። ልጅዎ ጤናማ የሆነ በራስ ችሎ የመመራት ስሜት እንዲያድርበት ለማድረግ መርዳት ይችላሉ። በራስ መተማመን በልጅዎ እድገት ላይ ጠቃሚ የሆነ ጉዳይ ነው። ህጻናት ከሁለት ዓመት እድሜ ጀምሮ ብዙ የራስ መተማመን መንፈስ ይኖራቸዋል። ታዲያ ከዚህ እድሜ ጀምሮ ህጻናት ስለኑሯቸው ቀላል ምርጫዎችን ማድረግ ይችሉ ዘንድ ማበረታታት ይገባዎታል።
ከህፃን ጋር መግባባት መቻላችንን መረዳት
አዲስ የተወለደን ህፃን ወደ ቤት በሚመጣበት ጊዜ ወላጆችም ሆን ህጻኑ የመደሰትና የፍርሀት ስሜት ሊኖራቸው ይችላል። አዲስ የተወለደ ህፃንን በምንከባከብበት ጊዜ ዋናው ትኩረት መስጠት የሚገባን የህፃኑ ፍላጎት መሟሏቱን እርግጠኛ መሆን አለብን።